መዝሙረ ዳዊት 112
112
1 #
መዝ. 1፥1-2፤ 119፥1-2፤ 128፥1። ሃሌ ሉያ።
ጌታን የሚፈራ፥
ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
2ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፥
የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥
ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
4 #
መዝ. 37፥6፤ 97፥11፤ ምሳ. 13፥9፤ ኢሳ. 58፥10። ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፥
መሓሪ፥ ርኅሩኅና ጻድቅ ነው።
5ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥
ነገሩንም በቀና መንገድ ይፈጽማል።
6 #
ምሳ. 10፥7፤ ጥበ. 8፥13። ለዘለዓለም አይናወጥም፥
የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።
7ክፉ ዜናን አይፈራም፥
ልቡ የጸና፥ በጌታም የታመነ ነው።
8በጠላቶቹ ላይ እስኪኮራ ድረስ
ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራምም።
9 #
ምሳ. 22፥9፤ 2ቆሮ. 9፥9። በተነ፥ ለችግረኞችም ሰጠ፥
ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል፥
ቀንዱም#112፥9 ኃይልም በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10ክፉ ሰውም አይቶት ይቈጣል፥
ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፥
የክፉዎች ምኞት ትጠፋለች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 112: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ