የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 113

113
1 # መዝ. 135፥1። ሃሌ ሉያ።
የጌታ አገልጋዮች ሆይ፥ አመስግኑት፥
የጌታንም ስም አመስግኑ።
2ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ
የጌታ ስም ቡሩክ ይሁን።
3 # ሚል. 1፥11። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ
የጌታ ስም ይመስገን።
4 # መዝ. 148፥13። ጌታ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ልዑል ነው፥
ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።
5እንደ ጌታ እንደ እግዚአብሔር የሚሆን ማን ነው?
በላይ የሚኖር፥
6 # መዝ. 89፥7-9። በሰማይና በምድር ያሉትን ለማየት ዝቅ የሚል፥
7-8 # መዝ. 107፥41፤ 1ሳሙ. 2፥7-8። ከመኰንኖች ጋር ከሕዝቡም መኰንኖች ጋር ያኖረው ዘንድ
ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥
ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፥
9 # 1ሳሙ. 2፥5፤ ኢሳ. 54፥1። መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥
ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።
ሃሌ ሉያ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ