የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 106

106
1 # መዝ. 100፥5፤ 107፥1፤ 1ዜ.መ. 16፥34፤ ኤር. 33፥11፤ ዳን. 3፥89። ሃሌ ሉያ፥
ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና
ጌታን አመስግኑ።
2የጌታን ታላላቅ ሥራዎች ማን ይናገራል?
ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ያሰማል?
3 # ኢሳ. 56፥1-2። ፍርድን የሚጠብቁ፥
ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው።
4 # መዝ. 25፥7፤ ነህ. 5፥19። አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበኝ፥
በመድኃኒትህም ጐብኘኝ፥
5የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥
በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥
ከርስትህም ጋር እኮራ ዘንድ።
6 # መዝ. 78፥11-17፤ ዘፀ. 14፥11፤ ዘሌ. 26፥40፤ 1ነገ. 8፥47፤ ባሮክ 2፥12፤ ዳን. 9፥5። ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአት ሠራን፥
ዐመፅንም፥ በደልንም።
7አባቶቻችን በግብጽ ሳሉ ተኣምራትህን አላስተዋሉም፥
የፍቅርህንም ብዛት አላሰቡም፥
በቀይ ባሕር ባለፉ ጊዜ ዐመፁብህ።
8 # ሕዝ. 36፥20-22። ስለ ስሙ፥ ኃይሉንም ለማስታወቅ
አዳናቸው።
9 # ዘፀ. 14፥21-31፤ ኢሳ. 50፥2፤ 63፥11-14፤ ናሆም 1፥4። ቀይ ባሕርን ገሠጸው፥ እርሱም ደረቀ፥
እንደ ምድረ በዳ በጥልቁ መራቸው።
10ከሚጠሉአቸውም እጅ አዳናቸው፥
ከጠላትም እጅ ተቤዣቸው።
11ያሳደዱአቸውንም ውኃ ዋጣቸው፥
ከእነርሱም አንድ አልቀረም።
12 # ዘፀ. 15፥1-21። በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥
ምስጋናውንም ዘመሩ።
13ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥
ምክሩን እንኳን አልጠበቁም።
14 # መዝ. 78፥18፤ ዘፀ. 15፥24፤ 16፥3፤ ዘኍ. 11፥1-6። በምድረ በዳም በምኞትን ተቃጠሉ፥
በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
15 # መዝ. 78፥26-31፤ ዘኍ. 11፥33። የለመኑትንም ሰጣቸው፥
ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።
16 # ዘኍ. 16፤ ዘዳ. 11፥6፤ ኢሳ. 26፥11። ሙሴንም፥ ጌታ የቀደሰውንም አሮንን
በሰፈር ተመቀኙአቸው።
17ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥
የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፥
18በማኅበራቸውም እሳት ነደደች፥
ነበልባም ክፉዎችን አቃጠላቸው።
19 # ዘፀ. 32፤ ዘዳ. 9፥8-21፤ ኤር. 2፥11፤ የሐዋ. 7፥41፤ ሮሜ 1፥23። በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥
ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
20ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ
ክብራቸውን ለወጡ።
21-22ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥
ድንቅንም በካም ምድር፥
ግሩም ነገርንም በቀይ ባሕር ያደረገውን
ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።
23 # ዘፀ. 32፥11፤ ዘዳ. 9፥25፤ ሕዝ. 22፥30። እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ
የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥
ያጠፋቸው እንደ ነበረ ተናገረ።
24 # ዘሌ. 26፥33፤ ዘኍ. 14፤ ዘዳ. 1፥25-36፤ ሕዝ. 20፥15፤23። የምትወደደውን ምድር ናቁ፥
በቃሉም አልታመኑም፥
25በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፥
የጌታን ቃል አልሰሙም።
26-27በምድረ በዳም ይጥላቸው ዘንድ፥
ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥
በየአገሩም ይበትናቸው ዘንድ፥
እጁን አነሣባቸው።
28 # ዘኍ. 25፤ ዘዳ. 26፥14፤ ሲራ. 45፥23-24። ከባዓል ፔዖርም ጋር ተጣበቁ#106፥28 ጣዖት አመለኩ።
የሙታንንም መሥዋዕት በሉ፥
29በሥራቸውም አስመረሩት፥
ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
30ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥
ቸነፈሩም ተወ፥
31ያም እስከ ዘለዓለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
32-33 # መዝ. 95፥8-9፤ ዘፀ. 17፥1-7፤ ዘኍ. 20፥2-13፤ ዘዳ. 6፥16፤ 33፥8። በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥
መንፈሱን አስመርረዋታልና፥
በእነርሱም የተነሣ ሙሴ ተበሳጨ፥
በከንፈሮቹም ያለማስተዋል ተናገረ።
34 # ዘዳ. 7፥1፤ መሳ. 2፥1-5። ጌታ እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፥
35 # ዘሌ. 18፥3፤ መሳ. 1፥27-35፤ 3፥5። ከአሕዛብም ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
36 # ዘሌ. 18፥21፤ ዘኍ. 35፥33፤ ዘዳ. 32፥17፤ መሳ. 2፥11-13፤17፤19፤ 2ነገ. 16፥3፤ ባሮክ 4፥7፤ 1ቆሮ. 10፥20። ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ ወጥመድም ሆኑባቸው።
37ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ፥
38የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸን ደም፥
ለከነዓን ጣዖቶች የሠዉአቸውን ንጹሕ ደም አፈሰሱ፥
ምድርም በደም ረከሰች።
39በሥራቸው ረከሱ፥
በድርጊታቸውም አመነዘሩ።
40የጌታም ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፥
ርስቱንም ተጸየፈ።
41 # መሳ. 2፥14-23። በአሕዛብም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥
የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።
42ጠላቶቻቸውም ግፍ አደረጉባቸው፥
ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።
43 # ኢሳ. 63፥7-9። ብዙ ጊዜ አዳናቸው፥
እነርሱ ግን በምክራቸው አስመረሩት፥
በስሕተታቸውም ተዋረዱ።
44እርሱ ግን ጩኸታቸውን በሰማ ጊዜ
ጭንቃቸውን ተመለከተ፥
45 # ዘሌ. 26፥42። ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥
እንደ ጽኑ ፍቅሩም ብዛት ተጸጸተ።
46በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።
47 # 1ዜ.መ. 16፥35። ጌታ አምላካችን ሆይ፥ አድነን፥
ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥
በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥
ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።
48 # መዝ. 41፥14፤ 72፥18፤ 89፥53፤ 1ዜ.መ. 16፥36፤ ነህ. 9፥5። ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ፥
ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል። ሃሌ ሉያ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ