የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 11

11
1የሐሰት ሚዛን በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፥
እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።
2ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፥
በትሑታን ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።
3ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፥
ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው ታጠፋቸዋለች።
4በቁጣ ቀን ሀብት አትረባም፥
ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።
5የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፥
ክፉ ግን በክፋቱ ይወድቃል።
6ቅኖችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፥
ወስላቶች ግን በምኞታቸው ይጠመዳሉ።
7ክፉ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋው ይቈረጣል፥
የኃያል አለኝታም ይጠፋል።
8ጻድቅ ከጭንቀት ይድናል፥
ክፉ ግን የእርሱን ቦታ ይወስዳል።
9እኩይ ሰው በአፉ ባልንጀራውን ያጠፋል፥
ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናሉ።
10በጻድቃን ልማት ከተማ ደስ ይላታል፥
በክፉዎችም ጥፋት እልል ትላለች።
11በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፥
በክፉዎች አፍ ግን ትገለበጣለች።
12ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥
አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።
13ለሐሜት የሚሄድ ምሥጢሩን ይገልጣል፥
በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል።
14 # ጥበ. 6፥24። መልካም ምክር በሌለበት ሕዝብ ይወድቃል፥
በአማካሪዎች ብዛት ግን ዋስትና ይገኛል።
15ለእንግዳ ሰው የሚዋስ ክፉ መከራን ይቀበላል፥
ዋስ መሆንን የሚጠላ ግን ይድናል።
16ሞገስ ያላት ሴት ክብርን ታገኛለች፥
ኃያላንም ሀብትን ያገኛሉ።።
17ቸር ሰው ለራሱ መልካም ያደርጋል፥
ጨካኝ ግን ራሱን ይጐዳል።
18ክፉ ሰው የሐሰት ደመወዝ ያገኛል፥
ጽድቅን የሚዘራ ግን የታመነ ዋጋ አለው።
19በጽድቅ የሚጸና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፥
ክፋትን የሚከተል ግን ወደ ሞት ይሄዳል።
20ልበ ጠማሞች በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው፥
በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው።
21ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥
የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።
22በዐሣማ አፍንጫ ላይ የወርቅ ቀለበት፥
ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴት።
23የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፥
የክፉዎች ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው።
24በልግስና የሚሰጥ#11፥24 መዝ 112፥ 9 ተመ.። ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፥
ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።
25በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥
ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል።
26እህልን የሚደብቅ#11፥26 በውድ ዋጋ ለመሸጥ ሰው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፥
በረከት ግን በሚሸጠው ራስ ላይ ነው።
27መልካምን ተግቶ የሚሻ ደስታን ይፈልጋል፥
ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል።
28በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፥
ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።
29ቤቱን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥
አላዋቂም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።
30የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥
ነፍሶችንም የሚማርክ እርሱ ጠቢብ ነው#11፥30 ግሪኩ “የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በድንገት ይወገዳሉ” ይላል።
31 # 1ጴጥ. 4፥18። እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ ፍዳውን የሚቀበል ከሆነ፥
ይልቁንስ ክፉዎችና ዓመፀኞችስ እንዴት ይሆኑ!

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ