1
መጽሐፈ ምሳሌ 11:25
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥ ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 11:24
በልግስና የሚሰጥ ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፥ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 11:2
ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፥ በትሑታን ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 11:14
መልካም ምክር በሌለበት ሕዝብ ይወድቃል፥ በአማካሪዎች ብዛት ግን ዋስትና ይገኛል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 11:30
የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፥ ነፍሶችንም የሚማርክ እርሱ ጠቢብ ነው።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 11:13
ለሐሜት የሚሄድ ምሥጢሩን ይገልጣል፥ በመንፈስ የታመነ ግን ነገሩን ይሰውራል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 11:17
ቸር ሰው ለራሱ መልካም ያደርጋል፥ ጨካኝ ግን ራሱን ይጐዳል።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 11:28
በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፥ ጻድቃን ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 11:4
በቁጣ ቀን ሀብት አትረባም፥ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።
10
መጽሐፈ ምሳሌ 11:3
ቅኖች ቅንነታቸው ትመራቸዋለች፥ ወስላቶችን ግን ጠማማነታቸው ታጠፋቸዋለች።
11
መጽሐፈ ምሳሌ 11:22
በዐሣማ አፍንጫ ላይ የወርቅ ቀለበት፥ ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴት።
12
መጽሐፈ ምሳሌ 11:1
የሐሰት ሚዛን በጌታ ፊት አስጸያፊ ነው፥ እውነተኛ ሚዛን ግን ደስ ያሰኘዋል።
Home
Bible
Plans
Videos