ኦሪት ዘኍልቊ 7:1-10

ኦሪት ዘኍልቊ 7:1-10 መቅካእኤ

እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ማደሪያውን ተክሎ ከጨረሰ በኋላ፥ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፤ ከተቈጠሩት በላይ የተሾሙት የነገዶች አለቆች የነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ቁርባናቸውን አቀረቡ። መባቸውንም በጌታ ፊት አመጡ፥ የተሸፈኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ ለሁለትም አለቆች ለእያንዳንዳቸው አንድ ሠረገላ ለእያንዳንዱም አለቃ አንዳንድ በሬ አመጡ፤ በማደሪያው ፊት አቀረቡ። ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለመገናኛው ድንኳን መገልገያ እንዲሆኑ እነዚህን ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገልግሎታቸው ትሰጣቸዋለህ።” ሙሴም ሰረገሎቹንና በሬዎቹን ተቀብሎ ለሌዋውያን ሰጣቸው። ለጌድሶን ልጆች እንደ አገልግሎታቸው ሁለት ሰረገሎችንና አራት በሬዎችን ሰጣቸው። በካህኑም በአሮን ልጅ በኢታምር ቁጥጥ ሥር ሆነው ለሜራሪ ልጆች እንደ አገልግሎታቸው አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጣቸው። ለቀዓት ልጆች ግን በትከሻቸው በመሸከም ቅዱስ የሆኑትን ነገረሮች ማገልገል የእነርሱ ነበርና፥ ለእነርሱ ምንም አልሰጣቸውም። መሠዊያውም በተቀባ ቀን አለቆቹ መሠዊያውን ለመቀደስ ቁርባንን አቀረቡ፤ አለቆችም መባቸውን በመሠዊያው ፊት አቀረቡ።