ኦሪት ዘሌዋውያን 5
5
1 #
መሳ. 17፥2-3፤ ምሳ. 29፥24። “ማንም ሰው የመሓላን ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ ወይም ስለ ነገሩ አይቶ ወይም አውቆ ባይናገር፥ ኃጢአት መሥራቱ ነውና በደሉን ይሸከማል። 2#ዘሌ. 11፥1-45፤ 15፥31፤ 17፥15-16።ማንም ሰው ማንኛውንም ርኩስ ነገር ማለትም የረከሰ አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም በደረቱ እየተሳበ የሚርመሰመስ የረከሰ ፍጥረት በድን ሳይታወቀው ቢነካ፥ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ በደለኛም ነው፤ 3#ዘሌ. 12፥4፤ 13፥35-36፤ 15፥2-12፤ 19—27፤ ዘኍ. 19፥14-22።ወይም የረከሰን ሰው በመንካት ከሚያረክስ ከማናቸውም ዓይነት ርኩሰት ሳይታወቀው ነክቶ ቢረክስ፥ ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደለኛ ይሆናል። 4#ዘኍ. 30፥3፤ መሳ. 11፥30-36፤ 1ሳሙ. 14፥24-30፤ ማር. 6፥23-26፤ የሐዋ. 23፥12።ማናቸውም ሰው ክፉን ወይም መልካምን ለማድረግ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፤ ሳያስብ የማለው ስለ ማናቸውም ነገር ቢሆን፤ ይህንንም ሳይታወቀው ቢያደርግ፤ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል። 5አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በአንዱ በደለኛ ቢሆን፥ የሠራውን ኃጢአት ይናዘዛል። 6ስለ ሠራው ኃጢአት ለጌታ የበደል መሥዋዕት ያመጣል፤ እርሱም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።
7 #
ዘሌ. 5፥11፤ 12፥8፤ 14፥21። “እርሱም ጠቦትን ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት ሌላውን ደግሞ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለጌታ ያመጣል። 8#ዘሌ. 1፥14-17።ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤ እርሱም አስቀድሞ ለኃጢአት መሥዋዕት የሆነውን ያቀርባል፥ ራሱንም ከአንገቱ ይቈለምመዋል፥ ነገር ግን አይቈርጠውም። 9ከኃጢአቱም መሥዋዕት ደም በመሠዊያው ግድግዳ ላይ ይረጨዋል፤ የተረፈውም ደም ከመሠዊያው በታች ይንጠፈጠፋል፤ እርሱ የኃጢአት መሥዋዕት ነው። 10እንደ ሥርዓቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
11 #
ዘሌ. 2፥1-3፤ ዘኍ. 5፥15። “እርሱም ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት እንደ ቁርባኑ አድርጎ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካም ዱቄት ለኃጢአት መሥዋዕት ያመጣል፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስበትም፥ ዕጣንም አይጨምርበትም። 12ወደ ካህኑም ያመጣዋል፥ ካህኑም መታሰቢያው እንዲሆን ከእርሱ እፍኝ ሙሉ ይወስዳል፥ ለጌታም በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱም የኃጢአት መሥዋዕት ነው። 13ካህኑም ከእነዚያ በአንዳቸው ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። እንደ እህል ቁርባንም እንዲሁ የተረፈው ለካህኑ ይሆናል።”
የበደል መሥዋዕት
14ጌታም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 15#ዘሌ. 7፥1-6፤ ዘኍ. 5፥5-8።“ማናቸውም ሰው ቢተላለፍ፥ ሳያውቅም ለጌታ በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኃጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለጌታ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያመጣል፤ ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ በብር ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ለበደል መሥዋዕት ያቀርበዋል።#ዘሌ. 22፥14። 16#ዘሌ. 22፥14፤ 27፥13፤ 15፤ 19፤ 27።በተቀደሰ ነገር ላይ ስለ ሠራው ኃጢአት ዕዳ ይከፍላል፥ በሚከፍለውም ዕዳ ላይ አምስት እጅ ይጨምርበታል፥ ለካህኑም ይሰጠዋል። ካህኑም በበደል መሥዋዕት አውራ በግ ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
17 #
መዝ. 19፥13፤ ኢዮብ 1፥5። “ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል። 18ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው እንደ ግምጋሜህ መጠን ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሠራው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። 19እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው፤ በእውነት በጌታ ፊት በደለኛ ነው።” #መዝ. 59፥13፤ ሆሴዕ 4፥2።
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 5: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ