የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘሌዋውያን 4

4
የኃጢአት መሥዋዕት
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 2#ዘሌ. 6፥17-23፤ ዘኍ. 15፥22-31።“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ማናቸውም ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራ፥ 3የተቀባውም ካህን ኃጢአት ሠርቶ በሕዝቡ ላይ በደል ቢያመጣ፥ ስለ ሠራው ኃጢአቱ ነውር የሌለበት ወይፈን ለጌታ ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል። 4#ዘሌ. 1፥4።ወይፈኑንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ በጌታ ፊት ያመጣዋል፤ እጁንም በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናል፥ ወይፈኑንም በጌታ ፊት ያርደዋል። 5የተቀባውም ካህን ከወይፈኑ ደም ወስዶ ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣዋል፤ 6#ዘሌ. 4፥17-18፤ 16፥16፤ 4፥25።ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በጌታ ፊት በመቅደሱ መጋረጃ ትዩዩ ደሙን ሰባት ጊዜ ይረጫል። 7ካህኑም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው መዐዛው ያማረ ዕጣን በሚታጠንበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ የተረፈውንም የወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል። 8ለኃጢአትም መሥዋዕት ከሚታረደው ወይፈን ስብን ሁሉ ይወስዳል፤ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ 9ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር፥ 10#ዘሌ. 3፥3።ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን እንደሚወሰደው ከወሰደ በኋላ፥ ካህኑ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል። 11የወይፈኑን ቆዳ፥ ሥጋውንም ሁሉ፥ ራሱንም፥ እግሮቹንም፥ ሆድ ዕቃውንም፥ ፈርሱንም፥ 12#ዘሌ. 6፥23።ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ አመድ ወደሚፈስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዳል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።
13“የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገሩም ከጉባኤው ፊት ቢሸሸግ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ሠርተው ቢበድሉ፥ 14የሠሩትም ኃጢአት ሲታወቅ ጉባኤው ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ከመንጋው ወይፈንን ያቀርባሉ፤ ወደ መገናኛውም ድንኳን ፊት ያመጡታል። 15የጉባኤውም ሽማግሌዎች እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ በጌታ ፊት ይጭናሉ፤ ወይፈኑም በጌታ ፊት ይታረዳል። 16የተቀባውም ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፤ 17ካህኑም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በጌታ ፊት በመጋረጃው ፊት ለፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። 18በመገናኛውም ድንኳን ውስጥ በጌታ ፊት ባለው በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ከደሙ ያደርጋል፤ ደሙንም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጅ ባለው የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል። 19ስቡንም ሁሉ ከእርሱ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። 20#ዘሌ. 1፥4።የኃጢአት መሥዋዕት በሆነው ወይፈን ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በዚህ ወይፈን ላይ ደግሞ ያደርጋል፤ እርሱም እንዲህ ያደርግበታል፤ ካህኑም ስለ እነርሱ ያስተሰርያል፥ እነርሱም ይቅር ይባላሉ። 21#ዘሌ. 6፥23።ወይፈኑንም ከሰፈሩ ውጭ ይወስዳል፥ የፊተኛውንም ወይፈን እንዳቃጠለ ያቃጥለዋል፤ ይህ የማኅበሩ የኃጢአት መሥዋዕት ነው።
22 # ዘኍ. 10፥4፤ 25፥14። “አንድ ገዢም ኃጢአትን ቢሠራ፥ ጌታም አምላኩ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ አንዱን ባለማወቅ ሠርቶ ቢበድል፥ 23ለእርሱም የሠራው ኃጢአት የታወቀ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባት ፍየል ለቁርባኑ ያቀርባል፤ 24በፍየሉም ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ በጌታ ፊት ያርደዋል፤ እርሱ የኃጢአት መሥዋዕት ነው። 25#ዘሌ. 4፥30፤34፤ 8፥15፤ 9፥9፤ 16፥18፤ ዘፀ. 29፥12፤ ሕዝ. 43፥20፤ ዘሌ. 4፥7።ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፤ የተረፈውንም ደም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ በታች ያፈስሳል። 26ስቡንም ሁሉ እንደ አንድነት መሥዋዕት ስብ በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል። ካህኑም ኃጢአቱን ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
27 # ዘኍ. 15፥27፤28። “ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራና ቢበድል፥ 28ለእርሱም የሠራው ኃጢአት የታወቀ ቢሆን፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ነውር የሌለባትን እንስት ፍየል ለቁርባኑ ያመጣል። 29እጁንም የኃጢአት መሥዋዕት በሆነችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፤ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚታረድበት ስፍራ የኃጢአትን መሥዋዕት ያርዳል። 30ካህኑም ከደምዋ በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ የተረፈውንም ደምዋን ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሳል። 31ከአንድነት መሥዋዕት ላይ እንደተወሰደው ስብ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ ካህኑም ስለ እርሱ ያስተሰርያል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
32“ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት የበግ ጠቦት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለባትን እንስት ያመጣል። 33እጁንም የኃጢአት መሥዋዕት በሆነችው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ የሚቃጠልም መሥዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መሥዋዕት ያርዳታል። 34ካህኑም ከኃጢአት መሥዋዕት ደም በጣቱ ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ቀንዶች ላይ ያደርገዋል፥ የተረፈውንም ደምዋን ሁሉ ከመሠዊያው በታች ያፈስሳል። 35ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ጠቦት ላይ ስቡ እንደሚወሰድ እንዲሁ የእርሷን ስብ ሁሉ ይወስዳል፤ ካህኑም ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን ጋር በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ