ኦሪት ዘሌዋውያን 19

19
ሥርዓት እና የግብረ ገብ ቅድስና
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2#ዘሌ. 11፥44።“ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ። 3#ዘሌ. 20፥9፤ ዘፀ. 20፥12።ከእናንተ እያንዳንዱ ሰው እናቱንና አባቱን ያክብር፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ፥ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።#ዘሌ. 23፥3። 4#ዘሌ. 26፥1፤ ዘፀ. 20፥3-5፤ 34፥17፤ ዘዳ. 5፥8፤ 27፥15።ወደ ጣዖታትም ዘወር አትበሉ፥ ለራሳችሁም ይሆኑ ዘንድ ቀልጠው የተበጁትን የአማልክት ምስሎች አትሥሩ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
5“የአንድነትንም መሥዋዕት ለጌታ ስትሰዉ እንዲሠምርላችሁ አድርጋችሁ ሠዉት። 6መሥዋዕታችሁን በሠዋችሁበት ዕለትና በማግስቱ ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ማናቸውም ነገር ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። 7#ዘሌ. 7፥15-18።በሦስተኛውም ቀን ቢበላ ጸያፍ ነው፥ እርሱም ተቀበባይነት አይኖረውም፤ 8#ዘሌ. 7፥20።እርሱንም የሚበላ ማናቸውም ሰው ለጌታ የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና በደሉን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጠፋል።
9 # ዘሌ. 23፥22፤ ዘዳ. 24፥19-22። “የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። 10የወይንህንም ቃርሚያ አትቃርም፥ የወደቀውንም የወይንህን ፍሬ አትሰብስብ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተወው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
11 # ዘፀ. 20፥15-16። “አትስረቁ፥ አትካዱም፥ ከእናንተም ማንም ሰው ወንድሙን አያታልል። 12#ዘፀ. 20፥7፤ ማቴ. 5፥33-37።በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ በዚህም የአምላካችሁን ስም አታርክሱ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
13 # ዘዳ. 24፥14-15። “በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። ተቀጥሮ የሚያገለግለውን ሰው ደመወዙን እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አታቆይበት። 14#ዘዳ. 27፥18።መስማት የተሳነውን አትስደብ፥ በዓይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
15 # ዘፀ. 23፥2-3፤ ዘዳ. 1፥17፤ 16፥19፤ መዝ. 82፥2፤ ምሳ. 24፥23። “ፍርድን ፈጽሞ አታጓድሉ፤#19፥15 በፍርድ ፈጽሞ ፍትሕን አታዛቡ፤ በፍርድ በደልን ፈጽሞ አታድርጉ፤ የተዛባ ፍርድ ፈጽሞ አትስጡ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ። 16በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት ወድያና ወዲህ አትመላለስ፤ በባልንጀራህም ሕይወት#19፥16 ዕብራይስጡ ደም ይላል። ላይ መሰነናክል ሆነህ አትቁም፤#19፥16 ባልንጀራህ ሞት ተፈርዶበት ሳለ ሐቁን ብታውቅ ስለ ሕይወቱ ስትል እውነቱን መመስከር ይገባል የሚል ፍቺ ያለው ነው። ወይም ጥቅምን በመሸሻት በባልንጀራህ ደም ላይ አትቁም፤ እኔ ጌታ ነኝ።
17 # ማቴ. 18፥15፤ ሉቃ. 17፥3፤ ገላ. 6፥1። “ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው። 18#ማቴ. 5፥43፤ 19፥19፤ 22፥39፤ ማር. 12፥31፤ ሮሜ 13፥9፤ ገላ. 5፥14፤ ያዕ. 2፥8፤ 1ዮሐ. 3፥14።አትበቀል፥ በሕዝብህም ልጆች ላይ ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
19 # ዘዳ. 22፥9-12። “ሥርዓቴን ጠብቁ። እንስሳህን ከሌላ ዓይነት ዘር ጋር አታዳቅል፤ በእርሻህም ሁለት ዓይነት ዘር አትዝራ፤ ከሁለት ዓይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።”
20 # ዘዳ. 22፥22-29። “ማናቸውም ሰው በባርነት ሥር ካለች ሴት ጋር ቢተኛ፥ እርሷም ለሌላ ሰው ታጭታ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ያልተዋጀች ወይም አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ይህ አድራጎት ቅጣት ይረኖረዋል፤ ሆኖም አርነት አልወጣችምና አይገደሉም። 21#ዘሌ. 5፥14-19።እርሱም የበደሉን መሥዋዕት ይዞ ወደ ጌታ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይመጣል፥ ለበደልም መሥዋዕት አውራ በግ ያመጣል። 22ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት በጌታ ፊት የበደል መሥዋዕት በሆነው በግ ለእርሱ ያስተሰርይለታል፥ የሠራውም ኃጢአት ይቅር ይባላል።
23 # ዘዳ. 20፥19-20። “ወደ ምድሪቱም ገብታችሁ የሚበላ የፍሬ ዛፍ ሁሉ በተከላችሁ ጊዜ፥ ፍሬውን እንዳልተገረዘ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት ለእናንተ እንዳልተገረዘ ይሆናል፤#19፥23 ፍሬው እደተከለከለ ትቈጥሩታላችሁ፤ ሦስት ዓመት ለእናንተ የተከለከለ ይሆናል፤ አይበላም። 24የአራተኛውም ዓመት ፍሬ ሁሉ ለጌታ ምስጋና የተለየ ይሆናል። 25የተትረፈረፈም ፍሬ አብዝተው እንዲሰጡዋችሁ የአምስተኛውን ዓመት ፍሬ ብሉ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
26 # ዘሌ. 17፥10። “ከደሙ ጋር ምንም ዓይነት ነገር አትብሉ፤ ሞራ ገላጭም አትሁኑ፥ አስማትም አታድርጉ።#ዘዳ. 18፥10፤ 2ነገ. 17፥17፤ 21፥6፤ 2ዜ.መ. 33፥6። 27የራስ ጠጉራችሁንም ዙሪያውን አትከርክሙት፥ ጢማችሁንም ዙሪያውን አትቁረጡት። 28#ዘሌ. 21፥5።ስለ ሞተውም ብላችሁ ሥጋችሁን አትተልትሉ፥ ገላችሁንም ፈጽሞ አትንቀሱት፤ እኔ ጌታ ነኝ።
29 # ዘሌ. 21፥7፤ 14። “ምድሪቱ እንዳታመነዝር በበርኩስነትም እንዳትሞላ ሴት ልጅህን እንድታመነዝር አድርገሃት አታርክሳት። 30#ዘሌ. 19፥3።ሰንበታቴን ጠብቁ፥ ለመቅደሴም ክብርን ስጡ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
31 # ዘሌ. 20፥6፤ 27፤ ዘዳ. 18፥11፤ ኢሳ. 8፥19። “ወደ ሙታን መናፍስት ጠሪዎችና ወደ ጠንቋዮች አትሂዱ፤ በእነርሱም እንዳትረክሱ አትፈልጉአቸው፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
32“በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።
33 # ዘፀ. 22፥20፤ 23፥9፤ ኤር. 22፥3፤ ሚል. 3፥5። “በአገራችሁ ውስጥ ከእናንተ ጋር እንግዳ ቢቀመጥ ግፍ አታድርጉበት። 34#ዘዳ. 10፥19።እናንተ በግብጽ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገሩ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፥ እርሱንም እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱት፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
35“በፍርድ፥ በመለካትም፥ በመመዘንም፥ በመስፈርም አታታልሉ። 36#ዘዳ. 25፥13-16፤ ምሳ. 16፥11፤ አሞጽ 8፥5፤ ሚክ. 6፥10-11።ትክክለኛም ሚዛን፥ ትክክለኛም መመዘኛ፥ ትክክለኛም የኢፍ መስፈሪያ፥ ትክክለኛም የኢን መስፈሪያ ይኑሩአችሁ፤ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ። 37ሥርዓቴን ሁሉ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ አድርጉአቸውም፤ እኔ ጌታ ነኝ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ