መጽሐፈ ኢያሱ 12
12
በሙሴ የተያዙ ነገሥታት
1 #
ዘኍ. 21፥21-35፤ ዘዳ. 1፥4፤ 2፥24-37። የእስራኤልም ልጆች ያሸነፉአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን አገራቸውን የወረሱአቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ 2በሐሴቦን የተቀመጠው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፥ ይገዛ የነበረው በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ ሲሆን፥ 3#ኢያ. 13፥20።በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኪኔሬት ባሕር ድረስ፥ በቤትየሺሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፈስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር ነበር፤ 4#ዘኍ. 34፥11-12።ከራፋይምም ወገን የቀረ፥ በአስታሮትና በኤድራይ የተቀመጠው የባሳን ንጉሥ ዐግ፥ 5ይገዛ የነበረው የአርሞንዔምን ተራራ፥ ሰልካን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ ነበር። 6#ዘኍ. 32፥33፤ ዘዳ. 3፥12-13።የጌታ ባርያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የጌታም ባርያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
7ኢያሱና የእስራኤል ልጆች ያሸነፉአቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም የነበሩት በዮርዳኖስም ማዶ በምዕራብ በኩል በሊባኖስ ሸለቆ ካለችው ከበኣልጋድ ወደ ሴይር ተራራ እስከሚያወጣው እስከ ሐላቅ ተራራ ድረስ ኢያሱ በየድርሻቸው ርስት አድርጎ ለእስራኤል ነገድ በሰጣት ምድር፥ 8በተራራማው አገር፥ በቈላውም፥ በዓረባም፥ በቁልቁለቱም፥ በምድረ በዳውም፥ በደቡቡም ያሉ ኬጢያውያን አሞራውያንም ከነዓናውያንም ፌርዛውያንም ኤዊያውያንም ኢያቡሳውያንም ዘንድ ነበር። 9#ኢያ. 6፥2፤ 8፥23።የኢያሪኮ ንጉሥ፥ በቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፥ 10#ኢያ. 10፥23።የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ 11የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ 12#ኢያ. 10፥23፤33።የዔግሎም ንጉሥ፥ የጌዝር ንጉሥ፥ 13#ኢያ. 10፥38-39፤ 15፥36።የዳቤር ንጉሥ፥ የጌድር ንጉሥ፥ 14የሔርማ ንጉሥ፥ የዓድራ ንጉሥ፥ 15#ኢያ. 10፥29-30፤ 15፥35።የልብና ንጉሥ፥ የዓዶላም ንጉሥ፥ 16#ኢያ. 8፥17፤ 10፥28።የመቄዳ ንጉሥ፥ የቤቴል ንጉሥ፥ 17#ኢያ. 15፥34።የታጱዋ ንጉሥ፥ የኦፌር ንጉሥ፥ 18#ኢያ. 15፥53።የአፌቅ ንጉሥ፥ የለሸሮን ንጉሥ፥ 19#ኢያ. 11፥1፤ 10።የማዶን ንጉሥ፥ የአሦር ንጉሥ፥ 20#ኢያ. 11፥1።የሺምሮን ሚሮን ንጉሥ፥ የአክሻፍ ንጉሥ፥ 21#ኢያ. 17፥11።የታዕናክ ንጉሥ፥ የመጊዶ ንጉሥ፥ 22#ኢያ. 19፥37።የቃዴስ ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዮቅንዓም ንጉሥ፥ 23#ኢያ. 11፥2።በዶር ኮረብታ የነበረ የዶር ንጉሥ፥ በጌልገላ የነበረ የጎይም ንጉሥ፥ 24የቲርሳ ንጉሥ፥ ነገሥታቱ ሁሉ ሠላሳ አንድ ናቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ