የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢያሱ 11

11
በሰሜን በኩል የሚገኙ ከነዓናውያን ነገሥታት መሸነፋቸው
1እንዲህም ሆነ፤ የአሦር ንጉሥ ኢያቢስ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ማዶን ንጉሥ ወደ ዮባብ፥ ወደ ሺምሮንም ንጉሥ፥ ወደ አክሻፍም ንጉሥ፥ 2#ኢያ. 12፥3።በሰሜንም በተራራማው አገር፥ በኪኔሬትም ደቡብ በዓረባ፥ በቈላውም፥ በምዕራብም በኩል ባለ በዶር ኮረብታ ወደ ነበሩ ነገሥታት፥ 3#ኢያ. 3፥10።በምሥራቅና በምዕራብም ወዳለው ወደ ከነዓናዊው፥ ወደ አሞራዊውም፥ ወደ ኬጢያዊውም፥ ወደ ፌርዛዊውም፥ በተራራማውም አገር ወዳለው ወደ ኢያቡሳዊው፥ ከአርሞንዔምም በታች በምጽጳ ወዳለው ወደ ኤዊያዊው ላከ። 4#ዘፀ. 15፥1፤ 21።እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ፥ በቍጥር ም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ከሚሆን ብዙ ሕዝብ፥ እጅግም ከሚበዙ ፈረሶችና ሰረገሎች ጋር በመሆን ወጡ። 5እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እስራኤልን ለመውጋት መጡ፤ በማሮንም ውኃ አጠገብ በአንድ ላይ ሰፈሩ።
6ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ነገ በዚህ ጊዜ እኔ ሁሉንም እንደሞቱ አድርጌ በእስራኤል እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና አትፍራቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ትቈርጣለህ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት ታቃጥላለህ።” 7ኢያሱም ከተዋጊዎቹ ሁሉ ጋር በድንገት ወደ ማሮን ውኃ መጣባቸው፥ በእነርሱም ላይ ጥቃት ፈጸመ። 8#ኢያ. 13፥6።ጌታም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ አንድም ሳያስቀሩ መቱአቸው። 9ኢያሱም ጌታ እንዳዘዘው በእነሱ ላይ አደረገባቸው፤ የፈረሶቻቸውንም ቋንጃ ቈረጠ፥ ሰረገሎቻቸውንም በእሳት አቃጠለ።
10በዚያን ጊዜም ኢያሱ ተመልሶ አሦርን ያዘ፥ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ አሦርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች። 11በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም፤ አሦርንም በእሳት አቃጠላት። 12#ዘዳ. 7፥2፤ 20፥16-17።የጌታም ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ያዘ፥ በሰይፍም ስለት መታቸው፥ ፈጽሞም አጠፋቸው። 13ዳሩ ግን ኢያሱ ካቃጠላት ከአሦር ብቻ በቀር እስራኤል በኮረብቶቹ ላይ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ አላቃጠሉም። 14የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም። 15#ዘዳ. 7፥2፤ 31፥7-8።ጌታም ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፥ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም።
16 # ኢያ. 10፥41፤ 12፥8። ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ፥ ቈላውንም፥ ዓረባንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቈላውን ያዘ፥ 17#ኢያ. 12፥7፤ ዘዳ. 7፥24።ቈላውም እስከ ሴይር ከሚያወጣው ከሐላቅ ተራራ ጀምሮ ከአርሞንዔም ተራራ በታች በሊባኖስም ሸለቆ ውስጥ እስካለው እስከ በአልጋድ ድረስ ነበር፤ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ይዞ መታቸው፥ ገደላቸውም። 18ኢያሱም ብዙ ዘመን ከእነዚህ ነገሥታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር። 19#ኢያ. 9፥3፤ 7፤ 15።በገባዖን ከሚኖሩ ከኤዊያውያን በቀር ከእስራኤል ልጆች ጋር ዕርቅ ያደረገች አንዲት ከተማ አልነበረችም፤ ሁሉንም በጦርነት ድል አድርገው ያዙ። 20#ዘዳ. 2፥30፤ 20፥16-17።ጌታ ሙሴን እንዳዘዘ፥ እንዲያጠፉአቸው ምሕረትንም ሳያደርጉ ፈጽመው እንዲፈጅዋቸው፥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ልባቸውን እንዲያደነድኑ ከጌታ ዘንድ ሆነ።
21 # ኢያ. 15፥13-14፤ ዘኍ. 13፥22፤ ዘዳ. 1፥28፤ 9፥1-3። በዚያን ጊዜም ኢያሱ መጣ፥ ከተራራማውም አገር ከኬብሮንም ከዳቤርም ከአናብም ከእስራኤልም ተራራማ ሁሉ ከይሁዳም ተራራማ ሁሉ የዔናቅን ልጆች ገደለ፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው። 22በጋዛ በጌትም በአዛጦንም ጥቂቶች ቀሩ እንጂ በእስራኤል ልጆች ምድር ከዔናቅ ልጆች ማንም አልቀረም። 23#ኢያ. 14፥1—19፥51፤ ዘኍ. 34፥2-12፤ ዕብ. 4፥8-10።ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ