የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኢዩኤል 1

1
1ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው። 2እናንተ ሽማግሌዎች፥ ይህን ስሙ፤ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፥ አድምጡ። ይህ በዘመናችሁ ወይስ በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ነበርን? 3ይህን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው፥ ልጆቻቸውም ለኋለኛው ትውልድ ይንገሩ። 4ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።#1፥4 በአንበጣ ወረራ ምሳሌ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የተከሠተውን አሰቃቂ ወረራ ይገልጻል።
5አዲስ የወይን ጠጃችሁ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ ሰካራሞች፥ ነቅታችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የወይን ጠጅ የምትጠጡ ሁሉ፥ ዋይ በሉ። 6#ራእ. 9፥8።ቍጥር ም የሌለው ብርቱ ሕዝብ በምድሬ ላይ ወጥቶአልና፥ ጥርሳቸው እንደ አንበሳ ጥርስ፥ መንጋጋቸውም እንደ እንስቲቱ አንበሳ መንጋጋ ነው። 7ወይኔን ባዶ ምድር አደረገው፥ በለሴንም ሰበረው፥ ባዶም አደረገው፥ ጣለውም፥ ቅርንጫፎቹም ነጡ።
8እጮኛዋ ስለሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። 9የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከጌታ ቤት ተወግዶአል፥ የጌታ አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ። 10እህሉ ጠፍቶአልና፥ ወይኑም ደርቆአልና፥ ዘይቱም ጐድሎአልና እርሻው ምድረ በዳ ሆኖአል፥ ምድሪቱም አልቅሳለች። 11መከሩ ከእርሻ ጠፍቶአልና ገበሬዎች ሆይ፥ ስለ ስንዴውና ስለ ገብሱ እፈሩ፥ የወይን አትክልተኞችም አልቅሱ። 12ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል።
13የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ። 14ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ ሽምግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ ጌታ ቤት ሰብስቡ፥ ወደ ጌታም ጩኹ።
15 # ኢሳ. 13፥6። የጌታ ቀን ቀርቧልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል። 16ዓይናችን እያየ አይደለምን ከፊታችን ምግብ፥ ከአምላካችንም ቤት ደስታና እልልታ የጠፋው? 17ዘሩ በምድር ውስጥ ተበላሸ፥ እህሉ ደርቆአልና ጎተራዎቹ ባዶ ናቸው፥ ጎታዎቹም ፈርሰዋል። 18እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተቅበዘበዙ፥ የበግም መንጎች እየተሰቃዩ ነው። 19አቤቱ፥ እሳት የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና፥ ነበልባሉም የዱሩን ዛፍ ሁሉ አቃጥሎአልና ወደ አንተ እጮኻለሁ። 20ፈሳሹ ውኃ ደርቆአልና፥ እሳቱም የምድረ በዳውን ማሰማርያ በልቶአልና የምድር አራዊት ወደ አንተ አለኸለኹ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}