የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኢዩኤል መግቢያ

መግቢያ
ትንቢተ ኢዩኤል ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ወይም በአራተኛው ምእተ ዓመት አካባቢ ስለተከሠተው ሁኔታ የሚያስተምር መጽሐፍ ነው። ይህም የእግዚአብሔር ሕዝብ በፋርስ ዘመን የገጠመውን ተግዳሮት ያሳያል። ኢዩኤል በእስራኤል ምድር ታላቅ የአንበጣ መንጋ የሚመጣበትንና ብርቱ ጥፋት የሚያስከትል ድርቅ የሚከሠትበትን ጊዜ ይገልጣል፤ እነዚህ ሁኔታዎችም የጌታን ቀን መምጣት መቃረብ የሚያመለክቱ መሆኑን ይናገራል፤ የጌታም ቀን ሲመጣ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃዱን የሚቃወሙትን ሁሉ እንደሚቀጣ ጨምሮ ያስረዳል። ነቢዩ፥ ሕዝቡ ንስሓ እንዲገባ የእግዚአብሔርን ጥሪ በመግለጽ፥ ንስሐ ከገቡም ወደ ቀድሞው ሁኔታቸው በመመለስ እንደሚባርካቸው ያስገነዝባቸዋል። ከትንቢቱ ውስጥ ጐልቶ የሚታየው የተስፋ ቃል እግዚአብሔር በወንዶችና በሴቶች፥ በወጣቶችና በሽማግሌዎች ጭምር፥ በሕዝቡ ሁሉ ላይ መንፈሱን እንደሚያወርድ የሚገልጠው ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. አንበጣና የጠላት ጦር ሠራዊት (1፥1—2፥17)
2. የጌታ ቀን (2፥18-32)
3. ጌታ አሕዛብን እንደሚቀጣ (3፥1-21)
ምዕራፍ

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ