የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 20

20
1ናዕማታዊውም ሶፋር መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2“እንድመልስ ሐሳቤ ይገፋፋኝል፥ ስለዚህም ውስጤ መታገሥ አቅቶታል።
3የሚያሳፍረኝንም ተግሣጽ ሰምቻለሁ፥
የማስተዋሌም መንፈስ ይመልስልኛል።
4ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥
5የክፉ ሰዎች ፉከራ አጭር መሆኑን
አምላክን የሚክዱ ደስታቸው ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን?
6ከፍታው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥
ራሱም እስከ ደመና ቢደርስ፥
7እንደ ፋንድያ ለዘለዓለም ይጠፋል፥
ያዩትም፦ ወዴት ነው ያለው? ይላሉ።
8 # ጥበ. 5፥14። እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፥
እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል።
9ያየችውም ዐይን ዳግመኛ አታየውም፥
ለስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ ይሰወራል።
10ልጆቹ ድሆቹን ይክሳሉ፥
በገዛ እጆቹ ሀብቱን ይመልሳል።
11አጥንቶቹ በወጣት ኃይል ተሞልተው ነበር፥
ነገር ግን አሁን ያ የወጣትነት ኃይሉ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።”
12“ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥
ከምላሱም በታች ቢሰውረው፥
13ቢጠብቀውም ባይተወውም፥
በጉሮሮውም ቢይዘው፥
14መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፥
እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል።
15የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፥
እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል።
16የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፥
የእባብም ምላስ ይገድለዋል።
17ወንዞቹን አይመለከትም፥
የማሩንና የቅቤውን ጅረት አያይም።
18የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፥
እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም።
19ድሀውን ረግጦአል፥ ትቶታልም፥
ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።”
20“ሆዱ ዕረፍትን አላወቀምና
የወደደው ነገር አላዳነውም።
21እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፥
ስለዚህ በረከቱም አይጸናም።
22በጠገበ ጊዜ ይጨነቃል፥
የጉስቁልናም ሁሉ እጅ ታገኘዋለች።
23ሆዱን ሳያጠግብ
እግዚአብሔር የቁጣውን ትኩሳት ይሰድድበታል፥
በምግብ መልክም ያዘንብበታል።
24 # ጥበ. 5፥17-23። ከብረት መሣሪያም ቢሸሽ፥
የናስ ቀስት ይወጋዋል።
25እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፥
ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፥
ፍርሃትም ይወድቅበታል።
26ለከበሩ ዕቃዎቹ ጨለማ ተዘጋጅቶአል፥
በሰው እፍ ያልተባለች እሳት ትበላዋለች፥
በድንኳኑ ውስጥ የቀረውም ይጋያል።
27ሰማይ በደሉን ይገልጥበታል፥
ምድርም ትነሣበታለች።
28የቤቱም ንብረት ይሰናበታል፥
በቁጣው#20፥28 በአምላክ ቁጣ። ቀን በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል።
29ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥
ከአምላክ የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ