መጽሐፈ ኢዮብ 18
18
1ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2“እስከ መቼ ቃላትን ታበዛለህ?#18፥2 በዕብራይስጥ “ቃላትን ታጠምዳለህ” ይላል።
አስተውል፥ ከዚያም እኛ እንናገራለን።
3ስለ ምንስ እንደ እንስሶች ተቈጠርን?
ስለ ምንስ በዓይንህ ፊት ቀለልን?
4ቁጣ ወርሶሃል፥ ስለ አንተ ሲባል፥
ምድር ባድማ ትሆናለችን?
ወይስ ዓለት ከስፋራው ይነቀላልን?”
5 #
ኢዮብ 21፥17። “የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥
የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም።
6ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥
መብራቱም በላዩ ይጠፋል።
7የኃይሉም እርምጃ ትጠብባለች፥
ምክሩም ትጥለዋለች።
8እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፥
በመረብም ላይ ይሄዳል።
9አሽክላ ሰኰናውን ይይዛል፥
ወጥመድም ይበረታበታል።
10በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥
በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውራለች።
11ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥
በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።
12ኃይሉ በራብ ትደክማለች፥
መቅሠፍትም እስኪሰናከል ተዘጋጅቶለታል።
13የሰውነቱ ክፍሎች ይጠፋሉ፥
የሞትም የበኩር ልጅ ሰውነቱን ይበላል።
14ከሚታመንበት ድንኳን ይነቀላል፥
ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ያስቸኩሉታል።
15በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፥
በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።
16ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥
ጫፉም ከበላይ ይረግፋል።
17መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥
በሜዳም ስም አይቀርለትም።
18ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥
ከዓለምም ያሳድዱታል።
19ዘርም ትውልድም በሕዝቡ መካከል አይሆንለትም፥
በመኖሪያውም ውስጥ የሚቀመጥ ሰው አይቀርለትም።
20የፊተኞች ሰዎች እንደ ደነገጡ፥
እንዲሁ የኋለኞች ሰዎች ስለ ዘመኑ ይደነቃሉ።
21በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥
እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 18: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ