የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችን፥ በጎችንና እርግቦችን የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፤ እርግብ ሻጪዎችንም “ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት፤” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። ስለዚህ አይሁድ መልሰው “ይህንን ስለ ማድረግህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ፤” አላቸው። ስለዚህ አይሁድ “ይህ ቤተ መቅደስ ለአርባ ስድስት ዓመት እየተሠራ ነበር፤ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን?” አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ እየተናገረ ነበር። ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።
የዮሐንስ ወንጌል 2 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 2:13-22
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች