ዮሐንስ 2:13-22

ዮሐንስ 2:13-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የአ​ይ​ሁ​ድም የፋ​ሲ​ካ​ቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣ። በቤተ መቅ​ደ​ስም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ርግ​ቦ​ች​ንም የሚ​ሸ​ጡ​ትን፥ ገን​ዘብ ለዋ​ጮ​ች​ንም ተቀ​ም​ጠው አገኘ። የገ​መ​ድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ሁሉ​ንም ከቤተ መቅ​ደስ አስ​ወጣ፤ የለ​ዋ​ጮ​ች​ንም ገን​ዘብ በተነ፤ ገበ​ታ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገለ​በጠ። ርግብ ሻጮ​ች​ንም፥ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአ​ባ​ቴን ቤት የን​ግድ ቤት አታ​ድ​ርጉ” አላ​ቸው። ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “የቤ​ትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል ተጽፎ እን​ዳለ ዐሰቡ። አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ምን ምል​ክት ታሳ​ያ​ለህ?” አሉት። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን ቤተ መቅ​ደስ አፍ​ር​ሱት፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን አነ​ሣ​ዋ​ለሁ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው። አይ​ሁ​ድም፥ “ይህ ቤተ መቅ​ደስ በአ​ርባ ስድ​ስት ዓመት ተሠራ፤ አን​ተስ በሦ​ስት ቀኖች ውስጥ ታነ​ሣ​ዋ​ለ​ህን?” አሉት። እርሱ ግን ይህን የተ​ና​ገ​ረው ቤተ መቅ​ደስ ስለ ተባለ ሰው​ነቱ ነበር። ከሙ​ታን በተ​ነሣ ጊዜም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ እንደ ነገ​ራ​ቸው ዐሰቡ፤ በመ​ጻ​ሕ​ፍት ቃልና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ራ​ቸ​ውም ነገር አመኑ።

ዮሐንስ 2:13-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችን፥ በጎችንና እርግቦችን የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፤ እርግብ ሻጪዎችንም “ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት፤” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም “የቤትህ ቅንዓት ይበላኛል፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። ስለዚህ አይሁድ መልሰው “ይህንን ስለ ማድረግህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። ኢየሱስም መልሶ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ፤” አላቸው። ስለዚህ አይሁድ “ይህ ቤተ መቅደስ ለአርባ ስድስት ዓመት እየተሠራ ነበር፤ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን?” አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ እየተናገረ ነበር። ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

ዮሐንስ 2:13-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የአይሁድ ፋሲካም እንደ ተቃረበ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በቤተ መቅደስ ውስጥ ከብቶችን፣ በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡ እንዲሁም ተቀምጠው የገንዘብ ምንዛሪ የሚያከናውኑ ሰዎች አገኘ። የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ሁሉ ከቤተ መቅደሱ ግቢ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችን ሳንቲም በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለበጠ። ርግብ ሻጮችንም፣ “እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት!” አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “የቤትህ ቅናት ይበላኛል” ተብሎ የተጻፈው ትዝ አላቸው። አይሁድም፣ “ይህን ሁሉ ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ የሚያረጋግጥ ምን ታምራዊ ምልክት ታሳየናለህ?” አሉት። ኢየሱስም፣ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔም በሦስት ቀን መልሼ አነሣዋለሁ” ብሎ መለሰላቸው። አይሁድም፣ “ይህን ቤተ መቅደስ ለመሥራት አርባ ስድስት ዓመት ፈጅቷል፤ ታዲያ አንተ እንዴት በሦስት ቀን መልሰህ ታነሣዋለህ?” አሉት። ቤተ መቅደስ ሲል ግን፣ ስለ ገዛ ሰውነቱ መናገሩ ነበር። ከሙታንም ከተነሣ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ምን እንደ ተናገረ አስታወሱ፤ መጻሕፍትንና ኢየሱስ ያለውንም ቃል አመኑ።

ዮሐንስ 2:13-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የአይሁድ ፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለ ነበር ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ በቤተ መቅደስም በሬዎችን፥ በጎችንና ርግቦችን የሚሸጡትንና ገንዘብ ለዋጮችን ተቀምጠው ሲገበያዩ አገኘ። በዚህ ጊዜ የገመድ ጅራፍ አበጀና ሰዎችን ሁሉ፥ ከበጎችና ከበሬዎች ጋር ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ። ርግብ የሚሸጡትንም ሰዎች “ይህን ሁሉ ወዲያ ውሰዱ! የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት!” አላቸው። በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ “ስለ ቤትህ ያለኝ ቅናት እንደ እሳት አቃጠለኝ” ተብሎ እንደ ተጻፈ አስታወሱ። ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን፦ “አንተ ይህን ለማድረግ ሥልጣን እንዳለህ ምን ተአምር ታሳየናለህ?” አሉት። ኢየሱስም “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱትና እኔ በሦስት ቀን መልሼ እሠራዋለሁ” አላቸው። እነርሱም “ይህን ቤተ መቅደስ ለመሥራት አርባ ስድስት ዓመት ፈጅቶአል፤ ታዲያ አንተ በሦስት ቀን ውስጥ ትሠራዋለህን?” አሉት። ኢየሱስ ግን “ቤተ መቅደስ” ብሎ የተናገረው ስለ ሰውነቱ ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ ከሞት በተነሣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ይህን ተናግሮ እንደ ነበረ አስታወሱ፤ በዚህ ምክንያት በቅዱስ መጽሐፍ የተጻፈውንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

ዮሐንስ 2:13-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችንም በጎችን ግንቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፦ የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት። ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው። ስለዚህ አይሁድ፦ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።