አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ እንዲሁም ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና፥ ሥጋቸው በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት። ወታደሮችም መጥተው ከተሰቀሉት ሰዎች መካከል የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ቀድሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ። ያየውም መስክሮአል፤ ምስክርነቱም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንደሚናገር ያውቃል። ይህ የሆነው “ከእርሱ አጥንት አይሰበርም” የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው የመጽሐፍ ክፍል “ያንን የወጉትን ያዩታል” ይላል። ከዚህም በኋላ፥ አይሁድን በመፍራት በስውር የኢየሱስ ደቀመዝሙር የነበረው የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። እንዲሁም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቶ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ የአትክልት ቦታ ነበረ፤ በአትክልቱም ቦታ ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ። መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበረና የአይሁድ የዝግጅት ቀን ስለ ነበረ ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።
የዮሐንስ ወንጌል 19 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 19
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 19:31-42
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች