ትንቢተ ኤርምያስ 47
47
ፍልስጥኤም ላይ የተደረገ ፍርድ
1 #
ኢሳ. 14፥29-31፤ ሕዝ. 25፥15-17፤ ኢዮብ 3፥4-8፤ አሞጽ 1፥6-8፤ ሶፎ. 2፥4-7፤ ዘካ. 9፥5-7። ፈርዖንም ጋዛን ከመምታቱ በፊት ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው። 2“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። 3ከኃይለኞች ፈረሶቹ የኮቴያቸው ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መንጐድ፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው ዘወር ብለው አይመለከቱም። 4ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለመደምሰስ የተረፉትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና ለማጥፋት ስለሚመጣው ቀን ነው፤ ጌታ ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ትሩፍ ያጠፋልና። 5ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቷል፤ አስቀሎና በጸጥታ ተውጣለች፤ በሸለቆ ያላችሁ ትሩፋን ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትተለትላላችሁ? 6አንተ የጌታ ሰይፍ ሆይ! ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ ጸጥ ብለህም ዕረፍ። 7ጌታ ትእዛዝ ሰጥቶት እንዴት ዝም ይላል? በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ በዚያ አዘጋጅቶታል።”
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 47: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ