ትንቢተ ኢሳይያስ 63
63
የመቤዠትና የበቀል ቀን
1 #
ኢሳ. 34፥5-17፤ ኤር. 49፥7-22፤ ሕዝ. 25፥12-14፤ 35፥1-15፤ አሞጽ 1፥11-12፤ አብ. 1፥1-14፤ ሚል. 1፥2-5። ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።” 2“ቀሚስህ ስለምን ቀላ? ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለምን መሰለ?” 3#ራእ. 14፥20፤ 19፥15፤ ራእ. 19፥13።“መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ። 4የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፥ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና። 5#ኢሳ. 59፥16።ተመለከትሁ፥ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፥ ቁጣዬም አጸናኝ። 6በቁጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸውንም ምድር ላይ አፈሰስኩት።”
የእግዚአብሔር ምሕረት ሲታወስ
7ጌታ ስላደረገልን ሁሉ፥ የጌታን ቸርነትና የጌታን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን የተትረፈረፈ ጽኑ ፍቅር እናገራለሁ። 8እርሱም፦ “በእውነት ሕዝቤ፥ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች፥ ናቸው” አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው። 9በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።
10እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ፤ ስለዚህ ጠላታቸው ሆነ፤ እርሱ ራሱ ተዋጋቸው። 11እርሱም የቀደመውን ዘመን እንዲህ ብሎ አሰበ፦ የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለው? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለው? 12#ዘፀ. 14፥21።የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፥ ለራሱም የዘለዓለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፥ 13በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፥ በቀላይ ውስጥ ያለ እንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ? 14ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፥ እንዲሁ የጌታ መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው፤ እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።
የንስሐ ጸሎት
15ከሰማይ ተመልከት፥ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ለእኔ ተከለከለ? 16አብርሃም ባያውቀን፥ እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ ጌታ አንተ አባታችን ነህ፤ ስምህም ከዘለዓለም ታዳጊያችን ነው። 17አቤቱ ጌታ፥ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ አገልጋዮችህ ስትል ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ። 18የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም መቅደስን ረግጠውታል። 19ከዘለዓለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 63: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ