የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ዕዝራ 5

5
የቤተ መቅደሱ ዳግም መታነጽ መቀጠሉ
1 # ሐጌ 1፥1፤ ዘካ. 1፥1። ነቢያቱ ሐጌና የዒዶ ልጅ ዘካርያስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ለነበሩ አይሁድ በእነርሱ ላይ በነበረው በእስራኤል አምላክ ስም ትንቢት ተናገሩላቸው። 2#ሐጌ 1፥12፤ ዘካ. 4፥6-9።በዚያን ጊዜ የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ ተነሥተው በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመሩ፤ የሚያግዙአቸው የእግዚአብሔር ነቢያት ከእነርሱ ጋር ነበሩ። 3በዚያው ዘመን በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው ወደ እነርሱ መጥተው እንዲህ አሏቸው፦ “ይህን ቤት ለመሥራት፥ ቅጥሩንም ለማደስ ማን አዘዛችሁ?” 4ደግሞም፦ “ይህንስ ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ስም ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው። 5የአምላካቸው ዐይን ግን በአይሁድ ሽማግሌዎች ላይ ነበረ፥ ይህም ነገር ወደ ዳርዮስ እስኪደርስ ድረስ፥ መልሱም በደብዳቤ እስኪመጣ ድረስ አላስቆሙአቸውም።
6የደብዳቤውንም ግልባጭ በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው በወንዙ ማዶ የነበሩ ባለ ሥልጣናት ወደ ንጉሡ ዳርዮስ ላኩለት፤ 7እንዲህም የሚል ደብዳቤ ላኩለት፦ “ለንጉሡ ዳርዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤ 8ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል። 9እኛም ሽማግሌዎቹን፦ ‘ይህን ቤት እንድትሠሩ፥ ይህንንም ቅጥር እንድታድሱ ማን አዘዛችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው። 10ደግሞም እንድታውቅ፥ በእነርሱ ላይ ያሉትን መሪዎች ስም እንድንጽፍልህ ስማቸውን ጠየቅን። 11የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። 12#2ነገ. 25፥8-12፤ 2ዜ.መ. 36፥17-20፤ ኤር. 52፥12-15።ነገር ግን አባቶቻችን የሰማያትን አምላክ ስላስቆጡት በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ። 13#ዕዝ. 1፥2-11።ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሠሩ አዘዘ። 14ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያመጣውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሼሽባጻር ለተባለው፥ ገዢ ላደረገው ሰጠው፤ 15እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አስቀምጠው የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ’” አለው። 16በዚያን ጊዜ ይህ ሼሽባጻር መጣ፥ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ ነው አላለቀምም። 17“አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዐይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፥ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ