2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:6-9

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:6-9 መቅካእኤ

ስለዚህ ሁልጊዜ እንታመናለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ ብናውቅም፥ የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም። አዎ፥ ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በጌታ ዘንድ መኖር እንመርጣለን። ስለዚህ በማደሪያችን ሆንን ወይም ተለይተን ሄድን፥ እርሱን ደስ የምናሰኝ መሆንን ነው የምንፈልገው።