2 ቆሮንቶስ 5:6-9
2 ቆሮንቶስ 5:6-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በምድራዊ ሰውነታችን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ከጌታ የራቅን መሆናችንን ብናውቅም እንኳ ሁልጊዜ በእርሱ እንተማመናለን። እኛ የምንኖረውም ጌታን በማመን እንጂ እርሱን በማየት አይደለም። ከዚህ እንደ መኖሪያችን ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር ለመሆን እንመኛለን፤ ስለዚህ በመተማመን እንኖራለን። ከዚህ ከሥጋችን ጋር ብንሆንም ወይም ከእርሱ ብንለይም ዓላማችን ጌታን ማስደሰት ነው።
2 ቆሮንቶስ 5:6-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ፥ ጨክኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ፤ ከሥጋችሁም ተለይታችሁ ወደ ጌታችን ትሄዳላችሁ። በእምነት እንኖራለን፤ በማየትም አይደለም። ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል። አሁንም ብንኖርም፥ ብንሞትም እርሱን ደስ ለማሰኘት እንጥራለን።
2 ቆሮንቶስ 5:6-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ሁልጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤ ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም። ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋራ መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ። ስለዚህ በሥጋ ብንኖርም ወይም ከሥጋ ብንለይም ዐላማችን እርሱን ደስ ማሠኘት ነው።
2 ቆሮንቶስ 5:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል። ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን።