2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:5-8

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:5-8 መቅካእኤ

በእምነት እንደምትኖሩ ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ካልሆናችሁ በቀር፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ አታውቁም ኖሯል? እኛ ግን የማንበቃ እንዳልሆንን እንደምታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ። ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የበቃን ሆነን እንድንታይ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም የማንበቃ እንኳን ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን እንድታደርጉ ነው። ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልም።