2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7
7
ሰሎሞን ቤተ መቅደሱ እንዲቀደስ ማድረጉ
1 #
ዘሌ. 9፥23-24። ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላውን መሥዋዕት በላ፤ የጌታም ክብር ቤቱን ሞላ። 2የጌታም ክብር የጌታን ቤት ሞልቶት ነበርና ካህናቱ ወደ ጌታ ቤት መግባት አልቻሉም። 3#1ዜ.መ. 16፥34፤ 2ዜ.መ. 5፥13፤ ዕዝ. 3፥11፤ መዝ. 99፥5፤ 105፥1፤ 106፥1፤ 117፥1፤ 135፥1፤ ኤር. 40፥11።የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የጌታም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ እንዲህም ብለው ጌታን አመሰገኑ፦ “እርሱ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና።”
4ንጉሡም ሕዝቡም ሁሉ በጌታ ፊት መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። 5ንጉሡም ሰሎሞን ሀያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሀያ ሺህ በጎች ሠዋ። እንዲሁ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የጌታን ቤት ቀደሱ። 6ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ፦ ጽኑ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት ጌታን ለማመስገን የሠራውን የጌታን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር። 7ሰሎሞንም በጌታ ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን ውስጥ ቀደሰ፤ ሰሎሞን የሠራው የናስ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ስቡንም መያዝ አልቻለምና የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕት ስብ በዚያ አቀረበ።
8ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያሉ እስራኤል ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ። 9ሰባት ቀንም መሠዊያውን ቀድሰው፥ ሰባት ቀንም በዓል አድርገው ነበርና በስምንተኛው ቀን የተቀደሰውን ጉባኤ አደረጉ። 10በሰባተኛውም ወር በሃያ ሦስተኛውም ቀን ሕዝቡን ወደ ድንኳናቸው አሰናበተ፤ ጌታ ለዳዊትና ለሰሎሞን ለሕዝቡም ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ደስ ብሎአቸው ሐሴትን እያደረጉ ሄዱ።
11ሰሎሞንም የጌታን ቤትና የንጉሡን ቤት ጨረሰ፤ በጌታ ቤትና በራሱ ቤት ለመሥራት በልቡ ያሰበውን ሁሉ አከናወነ።
ጌታ ለሰሎሞን ለሁተኛ ጊዜ መገለጡ
12ጌታም ለሰሎሞን በሌሊት ተገልጦ እንዲህ አለው፦ “ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ ይህንም ስፍራ ለራሴ ለመሥዋዕት ቤት መርጫለሁ። 13ዝናብ እንዳይወርድ ሰማያቱን ብዘጋ፥ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው፥ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ 14በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ። 15አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚጸለይ ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፥ ጆሮቼም ያደምጣሉ። 16አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ እንዲኖር ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ። 17አንተም ደግሞ አባትህ ዳዊት እንደ ሄደው በፊቴ ብትሄድ፥ እንዳዘዝሁህም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዓቴንና ፍርዴንም ብትጠብቅ፥ 18#1ነገ. 2፥4።ከአባትህ ከዳዊት ጋር፦ ‘በእስራኤል ላይ ገዢ የሚሆን ከዘርህ አይታጣም’ ብዬ ቃል ኪዳን እንዳደረግሁ የመንግሥትህን ዙፋን አጸናለሁ።
19“እናንተ ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁንም ሥርዓቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥ 20ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላችኋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ አርቄ እጥለዋለሁ፥ በአሕዛብም ሁሉ መካከል ምሳሌና መሳለቂያ አደርገዋለሁ። 21ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያዩ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ፦ ‘ጌታ በዚህ አገርና በዚህ ቤት ለምን እንዲህ አደረገ?’ ብለው ይደነቃሉ። 22መልሰውም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ ጌታን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው።’ ”
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ