1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 6
6
የሌዊ ትውልድ
1የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ። 2የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 3የእንበረምም ልጆች፤ አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም ነበሩ። የአሮን ልጆች፤ ናዳብ፥ አብዩድ፥ አልዓዛር፥ ኢታምር ነበሩ። 4አልዓዛር ፊንሐስን ወለደ፤ ፊንሐስ አቢሱን ወለደ፤ 5አቢሱም ቡቂን ወለደ፤ ቡቂም ኦዚን ወለደ፤ 6ኦዚም ዘራእያን ወለደ፤ ዘራእያም መራዮትን ወለደ፤ 7መራዮት አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 8አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪማአስን ወለደ፤ 9አኪማአስም ዓዛርያስን ወለደ፤ ዓዛርያስም ዮሐናንን ወለደ፤ 10ዮሐናንም ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በሠራው ቤት በክህነት ያገለግል ነበረ፤ 11ዓዛርያስም አማርያን ወለደ፤ አማርያም አኪጦብን ወለደ፤ 12አኪጦብም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም ሰሎምን ወለደ፤ 13ሰሎምም ኬልቅያስን ወለደ፤ ኬልቅያስም ዓዛርያስን ወለደ፤ 14ዓዛርያስም ሠራያን ወለደ፤ ሠራያም ኢዮሴዴቅን ወለደ፤ 15ጌታም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን በናቡከደነፆር እጅ ባስማረከ ጊዜ ኢዮሴዴቅ ተማርኮ ሄደ።
16 #
ዘፀ. 6፥16-19። የሌዊ ልጆች፤ ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ነበሩ። 17እነዚህም የጌድሶን ልጆች ስሞች ናቸው፤ ሎቤኒ እና ሰሜኢ። 18የቀዓትም ልጆች፤ እንበረም፥ ይስዓር፥ ኬብሮን፥ ዑዝኤል ነበሩ። 19የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው። 20ከጌድሶን፤ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ኢኤት፥ ልጁ ዛማት፥ 21ልጁ ዮአክ፥ ልጁ አዶ፥ ልጁ ዛራ፥ ልጁ ያትራይ ነበሩ። 22የቀዓት ልጆች፤ ልጁ አሚናዳብ፥ ልጁ ቆሬ፥ ልጁ አሴር፥ 23ልጁ ሕልቃና፥ ልጁ አቢሳፍ፥ ልጁ አሴር፥ 24ልጁ ኢኢት፥ ልጁ ኡርኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል ነበሩ። 25የሕልቃናም ልጆች፥ አማሢ፥ አኪሞት። 26የሕልቃናም ልጆች፤ ልጁ ሱፊ፥ ልጁ ናሐት፥ 27ልጁ ኤልያብ፥ ልጁ ይሮሐም፥ ልጁ ሕልቃና ነበሩ። 28የሳሙኤልም ልጆች፤ በኩሩ ኢዮኤል፥ ሁለተኛውም አብያ ነበሩ። 29የሜራሪ ልጆች፤ ሞሖሊ፥ ልጁ ሎቤኒ፥ ልጁ ሰሚኢ፥ ልጁ ዖዛ፥ 30ልጁ ሳምዓ፥ ልጁ ሐግያ፥ ልጁ ዓሣያ ነበሩ።
በንጉሥ ዳዊት የተሾሙት መዘምራን
31ዳዊትም ታቦቱ ዐርፎ ከተቀመጠ በኋላ በጌታ ቤት ያቆማቸው የመዘምራን አለቆች እነዚህ ናቸው። 32እነርሱም ሰሎሞን የጌታን ቤት በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ በመገናኛ ድንኳን ማደሪያ ፊት እያዜሙ ያገለግሉ ነበር፤ በየተራቸውም ያገለግሉ ነበር። 33አገልጋዮቹና ልጆቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓት ልጆች ዘማሪው ኤማን ነበረ፤ እርሱም የኢዮኤል ልጅ፥ የሳሙኤል ልጅ፥ 34የሕልቃና ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ የኤሊኤል ልጅ፥ የቶዋ ልጅ፥ 35የሱፍ ልጅ፥ የሕልቃና ልጅ፥ የመሐት ልጅ፥ የአማሢ ልጅ፥ 36የሕልቃና ልጅ፥ የኢዮኤል ልጅ፥ የዓዛርያስ ልጅ፥ የሶፎንያስ ልጅ፥ 37የታሐት ልጅ፥ የአሴር ልጅ፥ የአብያሳፍ ልጅ፥ የቆሬ ልጅ፥ 38የይስዓር ልጅ፥ የቀዓት ልጅ፥ የሌዊ ልጅ፥ የእስራኤል ልጅ ነበር። 39በቀኙም የቆመ ወንድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳፍም የበራክያ ልጅ፥ የሳምዓ ልጅ፥ 40የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፥ 41የኤትኒ ልጅ፥ የዛራ ልጅ፥ የዓዳያ ልጅ፥ 42የኤታን ልጅ፥ የዛማት ልጅ፥ የሰሜኢ ልጅ፥ 43የኢኤት ልጅ፥ የጌድሶን ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነበር። 44በግራቸውም በኩል ወንድሞቻቸው የሜራሪ ልጆች ነበሩ፤ ኤታን የቂሳ ልጅ፥ የአብዲ ልጅ፥ የማሎክ ልጅ፥ 45የሐሸብያ ልጅ፥ የአሜስያስ ልጅ፥ የኬልቅያስ ልጅ፥ 46የአማሲ ልጅ፥ የባኒ ልጅ፥ የሴሜር ልጅ፥ 47የሞሖሊ ልጅ፥ የሙሲ ልጅ፥ የሜራሪ ልጅ፥ የሌዊ ልጅ ነበር። 48ወንድሞቻቸውም ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ቤት ማደሪያ አገልግሎት ሁሉ ተሰጡ።
49አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአሔር ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ለማስተስረይ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር። 50የአሮንም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ልጁ አልዓዛር፥ ልጁ ፊንሐስ፥ ልጁ አቢሱ፥ 51ልጁ ቡቂ፥ ልጁ ኦዚ፥ ልጁ ዘራእያ፥ 52ልጁ መራዮት፥ ልጁ አማርያ፥ ልጁ አኪጦብ፥ 53ልጁ ሳዶቅ፥ ልጁ አኪማአስ።
ሌዋውያን የሰፈሩባቸው ስፍራዎች
54ማደሪያዎቻቸውም በየሰፈራቸው በየዳርቻቸው እነዚህ ናቸው፤ አንደኛው ዕጣ የወጣው ለአሮን ልጆች ለቀዓት ወገኖች ነበረ። 55ለእነርሱ በይሁዳ አገር ያለችውን ኬብሮንን፥ በእርሷ ዙሪያ የነበረውን መሰማሪያ ሰጡ፤ 56የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ሰጡ። 57ለአሮንም ልጆች እነዚህን የመማፀኛ ከተሞች ሰጡ፤ እርሱም፦ ኬብሮን፥ ልብናና መሰማሪያዋ፥ ደግሞ የቲር፥ ኤሽትሞዓና መሰማሪያዋ፥ 58ሖሎንና መሰማሪያዋ፥ ዳቤርና መሰማሪያዋ፥ 59ዓሳንና መሰማሪያዋ፥ ቤት-ሳሚስና መሰማሪያዋ ናቸው፤ 60እንዲሁም ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማሪያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓኖቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
61ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከነገዱ ወገን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 62ለጌድሶንም ልጆች በየወገናቸው ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ፥ ዐሥራ ሦስት ከተሞች ተሰጡ። 63ለሜራሪ ልጆች በየወገናቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ፥ ዐሥራ ሁለት ከተሞች በዕጣ ተሰጡ። 64የእስራኤልም ልጆች ለሌዋውያን ከተሞችን ከመሰማሪያዎቻቸው ጋር ሰጡ። 65ከይሁዳም ልጆች ነገድ፥ ከስምዖንም ልጆች ነገድ፥ ከብንያምም ልጆች ነገድ፥ እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ከተሞች በዕጣ ሰጡ።
66ከቀዓትም ልጆች ወገኖች ለአንዳንዶቹ ከኤፍሬም ነገድ ከተሞች ድርሻ ነበራቸው። 67እነዚህም የመማፀኛ ከተሞች ለእነርሱ ተሰጣቸው፤ እነርሱም፦ በተራራማው በኤፍሬም አገር ያለችውን ሴኬምና መሰማሪያዋ፥ ደግሞም ጌዝርና መሰማሪያዋ፥ 68ዮቅምዓምና መሰማሪያዋ፥ ቤት-ሖሮንና መሰማሪያዋ፥ 69ኤሎንና መሰማሪያዋ፥ ጋት-ሪሞንና መሰማሪያዋ ናቸው። 70እንዲሁም ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዓኔርንና መሰማሪያዋን፥ ቢልዓምንና መሰማሪያዋን፥ ከቀዓት ልጆች ወገን ለቀሩት ተሰጣቸው።
71ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ወገን በባሳን ያለችው ጎላንና መሰማሪያዋ፥ አስታሮትና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው፤ 72ከይሳኮርም ነገድ ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ዳብራትና መሰማሪያዋ፥ 73ራሞትና መሰማሪያዋ፥ ዓኔምና መሰማሪያዋ፤ 74ከአሴርም ነገድ መዓሳልና መሰማሪያዋ፥ ዓብዶንና መሰማሪያዋ፥ 75ሑቆቅና መሰማሪያዋ፥ ረአብና መሰማሪያዋ፤ 76ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቂርያታይምና መሰምርያዋ ተሰጣቸው።
77ከሌዋውያን ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ከዛብሎን ነገድ ሬሞንና መሰማሪያዋ፥ ታቦርና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው፤ 78እንዲሁም ከሮቤልም ነገድ በኢያሪኮ አንጻር በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል በምድረ በዳ ያለችው ቦሶርና መሰማሪያዋ፥ ያሳና መሰማሪያዋ፥ 79ቅዴሞትና መሰማሪያዋ፥ ሜፍዓትና መሰማሪያዋ፤ 80ከጋድም ነገድ በገለዓድ ያለችው ሬማትና መሰማሪያዋ፥ መሃናይምና መሰማሪያዋ፥ 81ሐሴቦንና መሰማሪያዋ፥ ኢያዜርና መሰማሪያዋ ተሰጣቸው።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ