የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:23-28

1ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል 16:23-28 መቅካእኤ

ምድር ሁሉ ጌታን አመስግኑ፤ ዕለት ዕለት ማዳኑን አውሩ። ክብሩን ለአሕዛብ፥ ተአምራቱንም ለሰዎች ሁሉ ንገሩ። ጌታ ታላቅ፥ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋልና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነው። የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ ጌታ ግን ሰማያትን ሠራ። ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ደስታ በስፍራው ውስጥ ናቸው። የአሕዛብ ወገኖች ለጌታ የሚገባውን ስጡ፥ ለጌታ ተገቢውን ክብርና ኃይል ስጡ።