የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 7:1-5

ትንቢተ ዘካርያስ 7:1-5 አማ05

ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ኪስሌው የተባለ ዘጠነኛው ወር በገባ በአራተኛው ቀን እግዚአብሔር ለዘካርያስ የነገረው ቃል ይህ ነው፤ የቤትኤል ነዋሪዎች ሣርኤጼርንና ሬጌሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላኩአቸው፤ የላኩአቸውም የእግዚአብሔር በረከት ይወርድ ዘንድ እንዲጸልዩና፥ የቤተ መቅደሱን ካህናትና ነቢያትን “እስከ አሁን ለብዙ ዓመቶች እንዳደረግነው በየአምስተኛው ወር በመጾም ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ ማዘናችንን እንቀጥልን?” ብለው እንዲጠይቁ ነበር። ከዚህም በኋላ ወደ እኔ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ “ባለፉት ሰባ ዓመቶች በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት እኔን ለማክበር ነበርን?