እኔ እንደ ሳሮን ጽጌረዳና በሸለቆ ውስጥ እንደሚበቅል የሱፍ አበባ ነኝ። ውዴ በሴቶች መካከል ስትታይ በእሾኽ መካከል እንደሚታይ የሱፍ አበባ ናት። ውዴ ከሌሎች ጐልማሶች ጋር ሲነጻጸር በዱር ዛፎች መካከል አምሮ እንደሚታይ የፖም ዛፍ ነው፤ እኔም እጅግ ደስ ብሎኝ በጥላው ሥር ዐረፍኩ፤ ጣፋጭ ፍሬውንም በመመገብ ተደሰትኩ። ወደ ምግብ አዳራሹ አስገባኝ፤ ፍቅሩንም እንደ ሰንደቅ ዓላማ በእኔ ላይ ከፍ ከፍ አደረገ። እኔ በፍቅሩ ተይዤ ስለ ታመምኩ ዘቢብ እየመገባችሁ አበረታቱኝ፤ በፖም ፍሬም አስደስቱኝ። ግራ እጁን ያንተርሰኛል፤ በቀኝ እጁም ያቅፈኛል።
መኃልየ መኃልይ 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መኃልየ መኃልይ 2:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች