ማሕልየ መሓልይ 2:1-6

ማሕልየ መሓልይ 2:1-6 NASV

እኔ የሳሮን ጽጌረዳ፣ የሸለቆም አበባ ነኝ። በእሾኽ መካከል እንዳለ ውብ አበባ፣ ውዴም በቈነጃጅት መካከል እንዲሁ ናት። በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኮይ፣ ውዴም በጕልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤ በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤ የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል። ወደ ግብዣው አዳራሽ ወሰደኝ፤ በእኔ ላይ ያለው ዐላማው ፍቅር ነው። በዘቢብ አበረታቱኝ፤ በእንኮይም አስደስቱኝ፤ በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና። ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ ቀኝ እጁም ዐቅፎኛል።