ደግሞም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “የእግዚአብሔር ቃል አጠገብህ ነው፤ እንዲያውም በአፍህና በልብህ ነው፤” ይህም ቃል እኛ የምናበሥረው የእምነት ቃል ነው። ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በአፍህ ብትመሰክርና እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣውም በልብህ ብታምን ትድናለህ። ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል፤ በቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፦ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።” እንግዲህ አንዱ ጌታ የሁሉም ጌታ ስለ ሆነ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ምንም ልዩነት የለም፤ እርሱም ለሚለምኑት ሁሉ በረከቱን አብዝቶ ይሰጣል፤ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” ተብሎአልና። ነገር ግን ሳያምኑበት እንዴት ሊጠሩት ይችላሉ? ስለ እርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምናሉ? ያለ አስተማሪስ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ? አስተማሪዎች ካልተላኩስ እንዴት ቃሉን ሊያስተምሩ ይችላሉ? ይህም “የመልካም ዜና አብሣሪዎች መምጣት እንዴት ደስ ያሰኛል!” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። ነገር ግን ኢሳይያስ፥ “ጌታ ሆይ! የተናገርነውን ቃል ማን ተቀበለ” ብሎ እንደ ተናገረ፥ ሁሉም የምሥራቹን ቃል አልተቀበሉም። ስለዚህ እምነት የሚገኘው የምሥራቹን ቃል ከመስማት ነው፤ የምሥራቹም ቃል የሚገኘው ስለ ክርስቶስ ከሚነገረው ትምህርት ነው።
ወደ ሮም ሰዎች 10 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮም ሰዎች 10:8-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች