የዮሐንስ ራእይ 19:1-7

የዮሐንስ ራእይ 19:1-7 አማ05

ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው! ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው፤ ምድርን በአመንዝራነትዋ ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ በፍርድ ቀጥቶአታል፤ እርስዋን በመቅጣትም የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።” እንደገናም፥ “ሃሌ ሉያ! ከእርስዋ የሚነሣው ጢስ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል!” እያሉ ጮኹ። ኻያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ በግንባራቸው ተደፍተው “አሜን፥ ሃሌ ሉያ!” እያሉ ሰገዱ። ከዚህ በኋላ “እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ታናናሾችም ታላላቆችም አምላካችንን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ። የብዙ ሰዎችን ድምፅ የወራጅ ውሃን ድምፅ፥ የብርቱ ነጐድጓድንም ድምፅ፥ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚችል ጌታ አምላካችን ይነግሣል! የበጉ ሠርግ ስለ ደረሰና የእርሱም ሙሽራ ስለ ተዘጋጀች ኑ ደስ ይበለን! ደስታም እናድርግ! እናክብረውም!