ራእይ 19:1-7

ራእይ 19:1-7 NASV

ከዚህ በኋላ የብዙ ሰዎችን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ማዳን፣ ክብርና ኀይል የአምላካችን ነው፤ ፍርዱ እውነትና ጽድቅ ነውና፤ በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን፣ ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባታል፤ ስለ ባሮቹም ደም ተበቅሏታል።” ደግሞም እንዲህ አሉ፤ “ሃሌ ሉያ! ጢስ ከርሷ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወጣል።” ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው አምላክ ወድቀው ሰገዱ፤ እንዲህም አሉ፤ “አሜን፣ ሃሌ ሉያ!” ከዚህ በኋላ እንዲህ የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ፤ “እናንተ ባሮቹ ሁሉ፣ እርሱን የምትፈሩ፣ ታናናሾችና ታላላቆችም፣ አምላካችንን አመስግኑ!” ደግሞም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ኀይለኛ ወራጅ ውሃ ድምፅ፣ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ የሚመስል እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን ቻይ ጌታ አምላካችን ነግሧልና። የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ፣ የእርሱም ሙሽራ ራሷን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ ክብርም እንስጠው።