የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 97

97
እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ነው
1እግዚአብሔር ንጉሥ ነው!
ምድር ሆይ ደስ ይበልሽ!
እናንተ በባሕር ውስጥ ያላችሁ ደሴቶች ሁሉ፥
ደስ ይበላችሁ!
2ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤
ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
3እሳት እፊት እፊቱ ይሄዳል፤
በዙሪያው ያሉትን ጠላቶቹን ያቃጥላል።
4መብረቁ በዓለም ላይ ያበራል፤
ምድርም አይታ ትንቀጠቀጣለች።
5በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ፊት፥
ተራራዎች እንደ ሰም ይቀልጣሉ።
6ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፤
ሕዝቦች ሁሉ ክብሩን ያያሉ።
7ለጣዖቶች የሚሰግዱና በእነርሱ የሚመኩ ሁሉ ያፍራሉ፤
እናንተ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
8አምላክ ሆይ!
ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤
የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ።
9እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል አምላክ ነህ፤
ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በሥልጣንህ ሥር ናቸው። #መዝ. 29፥1-2።
10እግዚአብሔር ክፉ ነገርን የሚጠሉትን ሁሉ ይወዳል፤
ታማኞች አገልጋዮቹን ያድናቸዋል፤
ከክፉ መንፈስ ኀይልም እንዲያመልጡ ያደርጋቸዋል።
11ብርሃን ለደጋግ ሰዎች፥
ደስታም ለልበ ቅኖች ይወጣላቸዋል።
12እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር
ጻድቃን ሁሉ ደስ ይበላችሁ!
ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ!

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ