መጽሐፈ መዝሙር 91:1-4

መጽሐፈ መዝሙር 91:1-4 አማ05

መጠለያ በመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ፥ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መጠጊያ የሚያደርግ፥ እግዚአብሔርን “አንተ መከታዬና መጠጊያዬ ነህ፤ አንተ የምተማመንብህ አምላኬ ነህ” ይለዋል። እግዚአብሔር ከተሰወሩ ወጥመዶችና ለሞት ከሚያደርሱ በሽታዎች ይጠብቅሃል። በጥበቃው ሥር ያደርግሃል። እርሱ ስለሚንከባከብህ በሰላም ትኖራለህ፤ የእርሱ ታማኝነት እንደ ጋሻ ወይም እንደ ከተማ ቅጽር ይሆንልሃል።