እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይኖራል፤ ዙፋኑንም ለፍርድ አዘጋጅቶአል። ዓለምን በፍትሕ ያስተዳድራል፤ ሕዝቦችንም በትክክል ይዳኛል። እግዚአብሔር ለተጨቈኑት መጠጊያ ነው፤ በመከራ ጊዜም መከላከያ አምባ ነው። አምላክ ሆይ! በአንተ የሚተማመኑትን ሁሉ ስለማትተዋቸው ስምህን የሚያውቁ ሁሉ ይተማመኑብሃል። በጽዮን ለሚኖር እግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! ያደረገውንም ድንቅ ሥራ ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ! እግዚአብሔር የተጨቈኑትን ያስታውሳል ጩኸታቸውን አይረሳም የሚበድሉአቸውንም ይቀጣል።
መጽሐፈ መዝሙር 9 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 9:7-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች