አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤ ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ። አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤ የተቀደሰ ዘይት ቀብቼም አነገሥኩት። እርሱን ለመርዳትና ለማበርታት፥ እኔ ዘወትር ከእርሱ ጋር ነኝ። ጠላት አይረታውም፤ ክፉም ሰው አያዋርደውም። ጠላቶቹን አደቅለታለሁ፤ የሚጠሉትንም ሁሉ ከፊቱ አጠፋለታለሁ። ታማኝነቴና ዘለዓለማዊ ፍቅሬ ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ይሆናል። በሥልጣኔም ብርቱ አደርገዋለሁ። ግዛቱንም በባሕርና በወንዞች ማዶ በሚገኘው ምድር ላይ አደርግለታለሁ። እርሱም ‘አንተ አባቴና አምላኬ ነህ፤ አንተ አምባዬና አዳኜ ነህ’ ይለኛል። ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ እንዲሆን የብኲርናን ማዕርግ እሰጠዋለሁ። ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፤ ከእርሱም ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ከቶ አይፈርስም። ዙፋኑ እንደ ሰማይ የጸና ይሆናል፤ ዘሩም ለዘለዓለም ይነግሣል። “ነገር ግን የእርሱ ዘሮች ሕጌን ቢጥሱ፥ በሥርዓቴም ባይኖሩ፤ ድንጋጌዎቼን ቢተላለፉና ትእዛዞቼን ባይጠብቁ፥ በኃጢአታቸው ምክንያት እቀጣቸዋለሁ፤ በበደላቸውም ምክንያት መከራ አመጣባቸዋለሁ። ነገር ግን ለዳዊት ያለኝ ፍቅር ከቶ አይገታም፤ ለእርሱ የሰጠሁትንም የተስፋ ቃል ከመፈጸም ወደ ኋላ አልልም። ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አላፈርስም፤ ለእርሱ ከሰጠሁትም የተስፋ ቃል አንዱን እንኳ አላስቀርም። “በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ በቅዱስ ስሜ ስለ ማልኩ ለዳዊት ከቶ አልዋሽም። ትውልዱ አይቋረጥም፤ መንግሥቱንም ፀሐይ እስከምትኖርበት ዘመን እጠብቃለሁ። በሰማይ በእውነተኛነት እንደምትመሰክረው እንደ ጨረቃም የጸና ይሆናል።”
መጽሐፈ መዝሙር 89 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 89:19-37
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች