በዚያ ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤ ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤ “ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤ ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት። ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁ፤ በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት። እጄ ይደግፈዋል፤ ክንዴም ያበረታዋል። በጠላት አይበለጥም፤ ክፉ ሰውም አይበግረውም። ባላንጣዎቹን በፊቱ አደቅቃቸዋለሁ፤ ጠላቶቹንም እቀጠቅጣለሁ። ታማኝነቴና ምሕረቴ ከርሱ ጋራ ይሆናል፤ በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል። እጁን በባሕር ላይ፣ ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ። እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤ አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል። እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤ ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል። ምሕረቴንም ለዘላለም ለርሱ እጠብቃለሁ፤ ከርሱ ጋራ የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል። የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣ ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ። “ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ ደንቤን ባይጠብቁ፣ ሥርዐቴን ቢጥሱ፣ ትእዛዜንም ባያከብሩ፣ ኀጢአታቸውን በበትር፣ በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ። ምሕረቴን ግን ከርሱ አላርቅም፤ ታማኝነቴንም አላጓድልበትም። ኪዳኔን አላፈርስም፤ ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም። አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣ ዳዊትን አልዋሸውም። የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣ ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤ በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣ እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።” ሴላ
መዝሙር 89 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 89
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 89:19-37
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች