መጽሐፈ መዝሙር 86:11-17

መጽሐፈ መዝሙር 86:11-17 አማ05

እግዚአብሔር ሆይ! የእውነት መንገድህን እከተል ዘንድ አስተምረኝ፤ ባልተከፋፈለ ልብም እንዳከብርህ አድርገኝ። ጌታ አምላኬ ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘለዓለም አከብራለሁ። ለእኔ የምታሳየው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እንዴት ታላቅ ነው! ወደ ሲኦል ጥልቀት ከመውረድ አዳንከኝ። አምላክ ሆይ! ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤ አንተን የማይፈሩ ጨካኞች ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን መሐሪና ርኅሩኅ ለቊጣ የዘገየህ፥ የተትረፈረፈ ፍቅርና ታማኝነት ያለህ አምላክ ነህ። ወደ እኔ ተመልሰህ ራራልኝ፤ ለእኔ ለአገልጋይህ ብርታትን ስጠኝ፤ እኔን የሴት አገልጋይህን ልጅ አድነኝ። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስለ ረዳኸኝና ስላጽናናኸኝ፥ ጠላቶቼ አይተው ያፍሩ ዘንድ፥ ለእኔ ሞገስን የመስጠት ምልክትህን አሳየኝ።