መዝሙር 86:11-17

መዝሙር 86:11-17 NASV

እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ በእውነትህም እሄዳለሁ፤ ስምህን እፈራ ዘንድ፣ ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ። ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤ ለእኔ ያሳየሃት ምሕረት ታላቅ ናትና፤ ነፍሴንም ከሲኦል ጥልቀት አውጥተሃል። አምላክ ሆይ፤ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል፤ የግፈኞችም ጉባኤ ነፍሴን ይሿታል፤ አንተንም ከምንም አልቈጠሩም። ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ ለቍጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ። ወደ እኔ ተመልከት፤ ማረኝም፤ ለባሪያህ ኀይልህን ስጥ፤ የሴት ባሪያህንም ልጅ አድን። የሚጠሉኝ አይተው ያፍሩ ዘንድ፣ የበጎነትህን ምልክት አሳየኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ረድተኸኛልና፤ አጽናንተኸኛልም።