መጽሐፈ መዝሙር 41:1-3

መጽሐፈ መዝሙር 41:1-3 አማ05

ድኾችን የሚረዱ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል። እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ በሕይወትም ያኖራቸዋል፤ በምድር ላይ ይባርካቸዋል፤ ለጠላቶቻቸውም አሳልፎ አይሰጣቸውም። ታመውም በተኙበት አልጋ ላይ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤ ጤንነታቸውንም ይመልስላቸዋል።