መዝሙር 41:1-3

መዝሙር 41:1-3 NASV

ብፁዕ ነው፤ ለድኾች የሚያስብ፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ይታደገዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤ በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ ለጠላቶቹም ምኞት አሳልፎ አይሰጠውም። ታምሞ ባለበት ዐልጋ ላይ እግዚአብሔር ይንከባከበዋል፤ በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል።