እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት። ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ። ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ። በአንደበቴ አዲስ መዝሙር፥ እርሱም ለአምላካችን የምስጋና መዝሙር አኖረ፤ ብዙዎች በፍርሃት ተመልክተው በእግዚአብሔርም ይታመናሉ። በእግዚአብሔር ብቻ የሚታመኑ፥ ወደ ጣዖቶች የማይመለሱ፥ ሐሰተኞች አማልክትን ከሚከተሉ ከዐመፀኞች ሰዎች ጋር የማይተባበሩ የተባረኩ ናቸው። እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! ብዙ አስደናቂ ነገሮችን አድርገህልናል፤ ከአንተ የሚወዳደር ማንም የለም፤ አንተ ለእኛ ያቀድክልንን መልካም ነገር ማንም ሊቈጥረው አይችልም፤ እኔ ስለ እነርሱ በዝርዝር ለመናገርና ለማውራት ብሞክር ቊጥራቸው እጅግ የበዛ ይሆንብኛል። አንተ መሥዋዕትንና መባን አትፈልግም፤ እንስሶች በመሠዊያ ላይ እንዲቃጠሉ፥ ወይም ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም፤ በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደረግኸኝ። ስለዚህ “ስለ እኔ በተጻፈው የሕግ መጽሐፍ መሠረት እነሆ እኔ መጥቻለሁ። አምላኬ ሆይ! ፈቃድህን መፈጸም እወዳለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው” አልኩ። በትልቁ ጉባኤ ፊት ትክክለኛውን ነገር ተናገርኩ፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እንደምታውቀው ቃሌን ከመናገር አልቈጥበውም። ደግነትህን በልቤ ውስጥ አልደብቅም፤ ስለ ታማኝነትህና ስለ አዳኝነትህ ተናግሬአለሁ፤ ከትልቁ ጉባኤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንና እውነተኛነትህን አልሰውርም።
መጽሐፈ መዝሙር 40 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 40:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos