የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 40:1-10

መዝሙር 40:1-10 NASV

እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ። ከሚውጥ ጕድጓድ፣ ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤ እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤ አካሄዴንም አጸና። ለአምላካችን የሚሆን ውዳሴ፣ አዲስ ዝማሬን በአፌ ላይ አኖረ፤ ብዙዎች ያያሉ፤ ይፈራሉም፤ በእግዚአብሔር ይታመናሉ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣ የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ ለእኛ ያቀድኸውን፣ ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፣ ስፍር ቍጥር አይኖረውም። መሥዋዕትንና ቍርባንን አልፈለግህም፤ ጆሮዎቼን ግን ከፈትህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትን፣ የኀጢአትንም መሥዋዕት አልሻህም። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ መጥቻለሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ተጽፏል፤ አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።” በታላቅ ጉባኤ ውስጥ ጽድቅን አበሠርሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ እንደምታውቀው፣ ከንፈሮቼን አልገጠምሁም። ጽድቅህን በልቤ አልሸሸግሁም፤ ታማኝነትህንና ማዳንህን እናገራለሁ፤ ምሕረትህንና እውነትህን፣ ከታላቅ ጉባኤ አልደበቅሁም።