እግዚአብሔር በሰው አካሄድ ከተደሰተ የእርምጃውን ትክክለኛነት ያረጋግጥለታል። እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም። ከወጣትነት እስከ ሽምግልና ኖሬአለሁ፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔር ደጉን ሰው ሲተወው፥ ልጆቹም ምግብ አጥተው ሲለምኑ፥ ከቶ አይቼ አላውቅም። ደግ ሰው ሁልጊዜ በልግሥና ይሰጣል፤ እንዲሁም ያበድራል፤ ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ። ከክፉ ነገር ራቅ፤ መልካም ነገርንም አድርግ፤ አንተም በሰላም ለዘለዓለም ትኖራለህ። እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድን ይወዳል፤ ታማኞቹንም አይተዋቸውም፤ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል፤ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ። ከጻድቅ ሰው አፍ ጥበብ ይወጣል፤ አንደበቱም ፍትሕን ይናገራል። የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም። ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል። እግዚአብሔር ግን በጠላቱ እጅ አሳልፎ አይሰጠውም፤ በአደባባይ ክርክርም እንዲሸነፍ አያደርገውም። ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፤ ትእዛዙንም ፈጽም፤ እርሱም ምድርን በማውረስ ያከብርሃል፤ ክፉዎች ሲወገዱም ታያለህ። አንድ ጨካኝና ክፉ ሰው በሀገሩ መሬት እንደ ለመለመ ዛፍ ተጠናክሮ አየሁ። ነገር ግን ቈይቼ ብመለስ ከስፍራው አጣሁት፤ ብፈልገውም ላገኘው አልቻልኩም። ደጉን ሰው ተመልከት፤ ቅን የሆነውንም ሰው እይ፤ ሰላም ወዳድ ሰው ዘር ይወጣለታል። ኃጢአተኞች ግን ፈጽሞ ይደመሰሳሉ፤ ዘራቸውም ይጠፋል። የጻድቃን መዳን የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው፤ በችግር ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው። እንዲጠብቃቸው በእርሱ ስለ ተማጸኑም ይረዳቸዋል፤ ያድናቸዋልም፤ ከክፉዎችም እጅ ይታደጋቸዋል።
መጽሐፈ መዝሙር 37 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 37:23-40
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos