የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 37:23-40

መዝሙር 37:23-40 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤ በመንገዱ ደስ ይለዋል። ቢሰናከልም አይወድቅም፣ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና። ጕልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤ ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣ ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም። ሁልጊዜ ቸር ነው፤ ያበድራልም፤ ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ። ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፣ ለዘላለምም ትኖራለህ። እግዚአብሔር ፍትሕን ይወድዳልና፣ ታማኞቹንም አይጥልም። ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤ የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በርሷም ለዘላለም ይኖራሉ። የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ አንደበቱም ፍትሓዊ ነገር ያወራል። የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤ አካሄዱም አይወላገድም። ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤ ሊገድሉትም ይሻሉ። እግዚአብሔር ግን በእጃቸው አይጥለውም፤ ፍርድ ፊት ሲቀርብም አሳልፎ አይሰጠውም። እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ። ክፉና ጨካኙን ሰው፣ እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤ ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤ ብፈልገውም አልተገኘም። ንጹሓንን ልብ በል፤ ቅኑንም አስተውል፤ የሰላም ሰው ተስፋ አለውና። ኀጢአተኞች ግን በአንድነት ይጠፋሉ፤ የክፉዎችም ዘር ይወገዳል። የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው። እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም፤ ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል፤ እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል።

መዝሙር 37:23-40 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር በሰው አካሄድ ከተደሰተ የእርምጃውን ትክክለኛነት ያረጋግጥለታል። እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም። ከወጣትነት እስከ ሽምግልና ኖሬአለሁ፤ ታዲያ፥ እግዚአብሔር ደጉን ሰው ሲተወው፥ ልጆቹም ምግብ አጥተው ሲለምኑ፥ ከቶ አይቼ አላውቅም። ደግ ሰው ሁልጊዜ በልግሥና ይሰጣል፤ እንዲሁም ያበድራል፤ ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ። ከክፉ ነገር ራቅ፤ መልካም ነገርንም አድርግ፤ አንተም በሰላም ለዘለዓለም ትኖራለህ። እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድን ይወዳል፤ ታማኞቹንም አይተዋቸውም፤ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል፤ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ። ከጻድቅ ሰው አፍ ጥበብ ይወጣል፤ አንደበቱም ፍትሕን ይናገራል። የአምላኩም ሕግ በልቡ ነው፤ እግሩም አይደናቀፍም። ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል። እግዚአብሔር ግን በጠላቱ እጅ አሳልፎ አይሰጠውም፤ በአደባባይ ክርክርም እንዲሸነፍ አያደርገውም። ተስፋህን በእግዚአብሔር ላይ አድርግ፤ ትእዛዙንም ፈጽም፤ እርሱም ምድርን በማውረስ ያከብርሃል፤ ክፉዎች ሲወገዱም ታያለህ። አንድ ጨካኝና ክፉ ሰው በሀገሩ መሬት እንደ ለመለመ ዛፍ ተጠናክሮ አየሁ። ነገር ግን ቈይቼ ብመለስ ከስፍራው አጣሁት፤ ብፈልገውም ላገኘው አልቻልኩም። ደጉን ሰው ተመልከት፤ ቅን የሆነውንም ሰው እይ፤ ሰላም ወዳድ ሰው ዘር ይወጣለታል። ኃጢአተኞች ግን ፈጽሞ ይደመሰሳሉ፤ ዘራቸውም ይጠፋል። የጻድቃን መዳን የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው፤ በችግር ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው። እንዲጠብቃቸው በእርሱ ስለ ተማጸኑም ይረዳቸዋል፤ ያድናቸዋልም፤ ከክፉዎችም እጅ ይታደጋቸዋል።

መዝሙር 37:23-40 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

መንገዱን በወደደ ጊዜ፥ የሰው አካሄድ በጌታ ይጸናል። ቢወድቅም አይጣልም፥ ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና። ጐለመስሁ አረጀሁም፥ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም። ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥ ዘሩም በበረከት ይኖራል። ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፥ ለዘለዓለምም ትኖራለህ። ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል። ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥ በእርሷም ለዘለዓለም ይኖራሉ። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያናገራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ በእርምጃውም አይሰናከልም። ክፉ ጻድቁን ይመለከተዋል፥ ሊገድለውም ይወድዳል። ጌታ ግን በእጁ አይተወውም፥ በፍርድም እንዲሸነፍ አይፈቅድም። በጌታ ተስፋ አድርግ፥ መንገዱንም ጠብቅ፥ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፥ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ። ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት፥ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም። ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፥ ለሰላም ሰው ተተኪ ይወጣለታልና። በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ፥ የክፉዎቸ ዘር ይጠፋል። የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው። ጌታ ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከከፉዎችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ በእርሱ ታምነዋልና።