መጽሐፈ መዝሙር 3
3
የስደት ጊዜ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶቼ እንዴት ብዙዎች ናቸው!
ብዙዎችም በጠላትነት በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤
2ብዙ ሰዎች “እግዚአብሔር አያድነውም” እያሉ
ስለ እኔ ይናገራሉ።
3እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤
ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ።
4ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤
እርሱም በተቀደሰ ተራራው ላይ ሆኖ ይሰማኛል።
5እኔ ተኛሁ፥ አንቀላፋሁም፤
እግዚአብሔር ሌሊቱን ሙሉ ስለ ጠበቀኝ
ከእንቅልፌ ተነሣሁ።
6በዙሪያዬ የከበቡኝን
በብዙ ሺህ የሚቈጠሩትን ጠላቶቼን አልፈራቸውም።
7ጌታ ሆይ! ተነሥ!
አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ!
የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤
ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ።
8ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። #2ሳሙ. 15፥13—17፥22።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 3: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997