መጽሐፈ መዝሙር 2
2
በእግዚአብሔር የተመረጠ ንጉሥ
1አሕዛብ ስለምን ያሤራሉ?
ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?
2እግዚአብሔርንና መሲሑን ለመቃወም
የዓለም ነገሥታት ተነሣሡ፤
ሹሞቻቸውም ከእነርሱ ጋር ተባበሩ። #ሐ.ሥ. 4፥25-26።
3“እግር ብረታቸውን ከእግራችን እንቊረጥ፤
ገመዳቸውን በጥሰን እንጣል” አሉ።
4በሰማይ ዙፋኑ ላይ የሚቀመጠው ይስቅባቸዋል፤
በከንቱ ሐሳባቸውም ጌታ ያፌዝባቸዋል።
5ከዚህ በኋላ በቊጣው ይገሥጻቸዋል፤
በመዓቱም ያስፈራራቸዋል።
6“በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ
ንጉሤን ሾምኩ” ይላቸዋል።
7“የእግዚአብሔርን ዐዋጅ ዐውጃለሁ፤
እርሱም እንዲህ አለኝ፦
‘አንተ ልጄ ነህ፤
እኔ ዛሬ ወለድኩህ፤ #ሐ.ሥ. 13፥33፤ ዕብ. 1፥5፤ 5፥5። 8ለምነኝ፤ አሕዛብ ሁሉ እንዲገዙልህ አደርጋለሁ፤
ምድርም በሙሉ የአንተ ርስት ትሆናለች።
9በብረት በትር ትሰብራቸዋለህ፤
እንደ ሸክላ ዕቃም ቀጥቅጠህ ታደቃቸዋለህ’ ” አለኝ። #ራዕ. 2፥26-27፤ 12፥5፤ 19፥15።
10እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤
እናንተ የምድር ገዢዎች ተጠንቀቁ።
11እግዚአብሔርን በፍርሃት አገልግሉት፤
በመንቀጥቀጥም ተገዙለት።
12ቊጣው በቅጽበት ስለሚነድ በእናንተ ላይ ተቈጥቶ እንዳያጠፋችሁ
በመንቀጥቀጥ ስገዱለት
እርሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997