አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ? እኔን ከማዳን የራቅኸው ለምንድን ነው? ከመቃተት ድምፄስ የራቅኸው ለምንድን ነው? አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም። ሆኖም አንተ በእስራኤል የተመሰገንክ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ የምትገዛ ቅዱስ አምላክ ነህ። የቀድሞ አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፤ በአንተም ስለ ተማመኑ አዳንካቸው። ለእርዳታ ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ አዳንካቸው፤ አንተን በተማመኑ ጊዜ አላሳፈርካቸውም። እኔ ግን ከሰው ሁሉ ያነስኩ ትል ነኝ፤ ሰዎች ያፌዙብኛል በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ። የሚያዩኝ ሰዎች ሁሉ ይዘባበቱብኛል፤ ፊታቸውን ያኰሳትሩብኛል፤ ራሳቸውንም ይነቀንቁብኛል። “እግዚአብሔር ያድነው ዘንድ በእርሱ ተማምኖአልና የሚወደው ከሆነ እስቲ ያድነው” ይላሉ። በደኅና እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ የእናቴን ጡት በምጠባበት በሕፃንነቴ ወራት እንኳ የጠበቅኸኝ አንተ ነህ።
መጽሐፈ መዝሙር 22 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 22:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች