መዝሙር 22:1-9
መዝሙር 22:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ? አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም። አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤ የእስራኤልም ምስጋና ነህ። አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው። ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤ በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም። እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ። የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤ ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤ “በእግዚአብሔር ተማምኗል፤ እንግዲህ እርሱ ያድነው፤ ደስ የተሠኘበትን፣ እስኪ ይታደገው።” አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤ በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።

መዝሙር 22:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ? እኔን ከማዳን የራቅኸው ለምንድን ነው? ከመቃተት ድምፄስ የራቅኸው ለምንድን ነው? አምላኬ ሆይ! በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አትሰማኝም፤ በሌሊት እጣራለሁ፤ ዕረፍትም የለኝም። ሆኖም አንተ በእስራኤል የተመሰገንክ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ የምትገዛ ቅዱስ አምላክ ነህ። የቀድሞ አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፤ በአንተም ስለ ተማመኑ አዳንካቸው። ለእርዳታ ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ አዳንካቸው፤ አንተን በተማመኑ ጊዜ አላሳፈርካቸውም። እኔ ግን ከሰው ሁሉ ያነስኩ ትል ነኝ፤ ሰዎች ያፌዙብኛል በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ። የሚያዩኝ ሰዎች ሁሉ ይዘባበቱብኛል፤ ፊታቸውን ያኰሳትሩብኛል፤ ራሳቸውንም ይነቀንቁብኛል። “እግዚአብሔር ያድነው ዘንድ በእርሱ ተማምኖአልና የሚወደው ከሆነ እስቲ ያድነው” ይላሉ። በደኅና እንድወለድ ያደረግኸኝ አንተ ነህ፤ የእናቴን ጡት በምጠባበት በሕፃንነቴ ወራት እንኳ የጠበቅኸኝ አንተ ነህ።
መዝሙር 22:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ለምን ራቅህ? አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፥ በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም። በእስራኤል ውዳሴዎች የምትኖር አንተ ግን ቅዱስ ነህ። አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፥ ተማመኑ አንተም አዳንሃቸው። ወደ አንተ ጮኹ አመለጡም፥ በአንተንም ተማመኑ አላፈሩም። እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፥ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ። የሚያዩኝ ሁሉ ያፌዙበኛል፥ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይሳለቃሉ፦ በጌታ ተማመነ፥ እርሱም ያድነው፥ ቢወድደውስ ያድነው።